ቢሮው በወቅታዊ የከተማችን የፀጥታ ጉዳዮች ላይ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው በወቅታዊ የከተማችን የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀመጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በወቅታዊ የከተማችን የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀመጠ።

የካቲት 03/06/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

******

የቢሮዉ ከፍተኛ አመራሮች ከተጠሪ ተቋም ደንብ ማስከበር አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የአፍሪካ ህብረት 39ኛዉን ጉባኤ አስመልክቶ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራዉ እንዲሁም አጠቃላይ በከተማችን ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ የእንግዳ ተቀባይነታችንን የሚያጎሉ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

ይህንን አስመልክቶ የቢሮዉ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 39ኛዉን የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ አስመልክቶ ከከተማው ነዋሪ ጋር ተከታታይነት ያላቸው ዉይይቶች መካሄድን ገልፀው፤ የፀጥታ ስምሪቱ የተጠናከረ እና አስተማማኝ ሲሆን የፀጥታ ጥምር ሀይሉ ደንብ ማስከበርን ጨምሮ እንዲሁም የሠላም ሠራዊቱ የምሽት የቀን ስምሪት ወስደዉ እየሠሩ መሆኑንም አያይዘው ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም ህብረተሠቡ የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በትብብር በመስራት በፍፁም እንግዳ ተቀባይነት ስሜት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፤ ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ችግሮችን ሲመለከት በመረጃ መስጫ ማእከሎቻችን 8882 አጭር የስልክ መስመርና በሲትዝን ኢንጌጅመንት አፕልኬሽን ፈጥነዉ መረጃ እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የከተማዉን የፀጥታ ሁኔታ የሚያዉኩ ድርጊቶችን በመከታተል እርምት እየተወሰደ መሆኑን ገልፀው ሺሻ መጠቀሚያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ጫት የሚቃምባቸዉ እና የወጣቱን ስነ ልቦና የሚጎድ ማንኛዉም ድርጊቶች የማስወገድ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይቱ ተነስቷል።