ወጣቱ ትውልድ በሰላም እሴት ግንባታ ላይ በመሳተ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ወጣቱ ትውልድ በሰላም እሴት ግንባታ ላይ በመሳተፍ የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ማጽናት እንደሚገባው ተገለፀ ።

ወጣቱ ትውልድ በሰላም እሴት ግንባታ ላይ በመሳተፍ የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ማጽናት እንደሚገባው ተገለፀ ።

የካቲት 3/2018 (አ.አ.ሰፀ.አስ.ቢሮ)

**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን "ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና " በሚል መሪ ቃል በብሎክ በወረዳና በክ/ከተማ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት ለሰላም እሴት ግንባታ ብሎም በሰላም አጠባበቅ ላይ ወጣቶች የራሳቸውን ሀላፊነት በመውሰድ ደረጃ ከፍተኛውን ድርሻ ይወጣሉ በማለት የሰለጠነ ወጣትን በመፍጠር በቀጣይ በሀገር ደረጃ የሚካሄደውን 7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ በመሳተፍና ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ፍትሀዊ የተሞላበት ሆኖ እንዲያልፍም በማድረግ የከተማዋን ሰላም ማጽናት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፤

የሰለጠነ ወጣት አርበኝነትን ያዋጀ ድህነትን ኋላ ቀርነትን ያለፈ ትርክትን የሚጸየፍ ሀገር ወዳድ ወጣት በማፍራት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየገሰገሰች ያለችበትን የብልጽግና መንገድ በማራመድ ወጣቱ የአንበሳውን ድርሻ የሚወጣ በውይይት በሀሳብ ልዕልና የሚያምን ሀሳብን በበላይነት የሚያሸንፍ ነጠላ ትርክትን ወደ ጎን በመተው በልማት በመልካም አስተዳደር ላይ ፊትአዉራሪ ሆኖ የሚዘልቅ የእኔነት ስሜት ያለው በስብዕና የተሞላ ወጣት መፍጠር ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

ኃላፊዋ አያይዘውም ወጣቱ ትውልድ ለጠላት የማይተኛ እርስ በርስ ከሚያጋጩ ሀሳቦችንና የጠላት ሀይሎች ሴራ ከውጭም ከውስጥም ያሉ የሀገርን አንድነት ሀሳብ ለመበታተን ሀሳባቸውን ከሚዘሩ ግለሰቦች በመራቅ በሁለንተናዊ ሀሳብ አንድ በመሆን ሀገራችን እየገሰገሰችበት ካለችበት ፈጣን የእድገት ደረጃ ጋር በመሆን አብሮነትን ለአለም ህዝብ ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ሀገር ወዳድ በመሆን የሀሳብ ጥቃትን በመመከት በጋራ በመቆም በሰላም አደረጃጀቱ ላይ በመሳተፍ ከተማው ላይ ስለ ሰላም በሚደረጉ ውይይቶች ላይ በመሳተፍ አካባቢን በመጠበቅ ከሀሰተኛ መረጃ በመራቅ ወጣቱ ትውልድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ አሳስበዋል ።

አቶ ክብረ አለም ደምሴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው በሀገር ውስጥ ሰላም መሆን ካልቻልን ለውጭ ሀገር ጠላት የመጋለጥ እድላችን ሰፊ እንደሚሆን በመረዳት የውጭ ሀገር ጠላትን በመመከት እንደ ሀገር ያለን ነገር በቂ በመሆኑ በሰላም እጦት ምክንያት እንዳናጣው በመጠንቀቅ በሰለጠነ አስተሳሰብ በመራመድ ለከተማችን ሰላም ዘብ ሆኖ በመቆም በተግባር የሚገለጽ ስራ ሰርቶ ማሳየት እንደሚገባ ተናግረዋል።

"ስልጡን ወጣት ለከተማ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና " በሚል ለወጣቶቹ የመወያያ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡቶ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።