የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው የውስጥ ለውስጥ መብራት የማስበራት ተግባርን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው የውስጥ ለውስጥ መብራት የማስበራት ተግባርን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የካቲት 03/2018 ዓ.ም (አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማዋ ውስጥ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ በማለም ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ግብረ ሀይሎችን በማቀናጀት የመብራት ማስበራት ተግባር ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል።
ቢሮው በቀሪዎቹ ክፍለ ከተሞችም ተግባሩን በማስቀጠል ላይ ሲሆን፣በዛሬው ዕለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገኘት የውስጥ ለውስጥ የመብራት ማስበራት ተግባር ከግብረ ሀይሎች ተሳትፎ ጋር ከዚህ ቀደም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ እና ወንጀል የሚከሰትባቸዉ ቦታዎች አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ብርሃናማ የሆኑ ስፍራዎችን ተዘዋውሮ የመስክ ምልከታ በማድረግ አፈፃፀሙን ገምግሟል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ በተደረገዉ ግምገማ በህዝብ ባለቤትነት ከጨለማ ወደ ብርሀን የተቀየሩ የውስጥ ለውስጥ ብሎኮች እና ቀጠናዎች፣ ለረጅም ጊዜ ሳይበሩ የነበሩ የመንገድ ዳር ፓሎች ከመብራት አገልግሎት ጋር በመተባበርና በማስጠገን እንዲበሩ የማድረግ ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተዘረጉ የሲሲቲቪ ካሜራዎችን በመግጠም የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ጸጥታ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊዋ አክለውም ማህበረሰቡ የደጅ መብራት የማውጣት ተግባር፣በአከባቢው የሰላምና የፀጥታ ሁኔታን ለማጠናከር እንዲሁም የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዝ እና ወንጀሎችን ለመቀነስ የሚረዳ መሆኑን አንስተዋል።
የአቃቂ ቃሊታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው እንደተናገሩት በህብረተሰቡ ተሳትፎ በእያንዳንዱ ብሎኮች ካሜራ በመግጠም፣የሚከሰቱ ወንጀሎችን የመቀነስና የቅድመ መከላከል ስራዎችን መስራት መቻላቸውን እና የክፍለ ከተማው የጸጥታ አካላት ከህዝቡ ጋር በመስራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፀጥታ አጠባበቅ ስራ እንዲኖር መደረጉን ተናግረዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት አሁን ጨለማ የሆኑ ቦታዎች ላይ በሁሉም ክ/ከተሞች ላይ እንዲበሩ መስራት፣የውስጥ ለውስጥ የመብራት ማስወጣት፣የማህበረሰብ አቀፍ ማዕከል ግንባታ ህዝቡን በማሳተፍ እና ቅኝጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር የሚል የቀጣይ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።
በመድረኩ ላይ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ ያሉ የሰላምና ፀጥታ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ፣ የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት፣ የፖሊስ እና የደንብ ማስከበር መዋቅር አመራሮችና ዳሬክተሮች እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።