የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ20...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የቀሪ 6 ወር የተከለሰ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የቀሪ 6 ወር የተከለሰ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የካቲት 4/2018 (አ.አ.ሰፀ.አስ.ቢሮ)

**

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ በተከለሰ የ2018 ዓ.ም በጀት አመት በቀሪ 6 ወራት ዕቅድ ላይ ከዘርፉ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ዘርፍ ያለው ሚና አይተኬ ነው ያሉት ኃላፊው ሰላምን ገንብቶ እሴትን በማምጣት ሂደት ውስጥ የአስተሳሰብ ልዕልናን በሰፊው በማየት በስራዎቻችን ላይ በሙሉ ዘላቂነት ያለው ስራ ለመስራት ህብረተሰቡን ማሳተፍ ተገቢም መሆን እንደሚገባው አብራርተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም ዘርፍ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ የሚገኝበት አንዱ ባለፉት ወራት በከተማው ላይ ሲካሄዱ የቆዩት በዓላቶች በሰላም መጠናቀቃቸው አንዱ ማሳያም እንደሆነ ገልጸው ለዚህም ባለሞያዎቹ ላሳዩት ተሳትፎ ምስጋናን አቅርበው ተቀናጅቶ የመስራት ውጤቱ አመርቂ እንደሆነ ሁሉ አግባብነት ባለው መልኩ ስራዎች ላይ በማተኮር የቢሮውንም የዘርፍንም ራዕይ ማሳካት እንደሚገባም ጭምር ተናግረዋል።

የዘርፉን የቀጣይ የስድስት ወራት የተከለሰ ዕቅድ ያቀረቡት አቶ ሙሉቀን እንየው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታና ብዝሀነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ዕቅድ ላይ ሰፊ ሀሳብና አስተያየት ከተሰጠ በኋላ በቀጣይ ጊዜያትም ዘርፉ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት አቶ ብርሀኑ ረታ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠው ውይይቱ ተጠናቋል ።