ቢሮው ከፌደራል ፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ከፌደራል ፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን ስለ ከተማው ሰላም ጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ጊዜያት በጥናት ደረጃ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ፡፡

ቢሮው ከፌደራል ፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን ስለ ከተማው ሰላም ጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ጊዜያት በጥናት ደረጃ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረገ፡፡

የካቲት 4/2018 (አ.አ.ሰፀ.አስ.ቢሮ)

********

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን ስለ ከተማው ሰላም ጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ለብሔራዊ ገጽታ ግንባታ ዕድሎች አደጋዎች እና የወደፊት እይታዎች ላይ በሚጠና ጥናት ላይ ውይይት አካሄዷል።

ዶ/ር ጥላሁን ተፈራ የፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪና የመልካም አስተዳደር የምርምር ማዕከል አስተባባሪ በከተማው ሰላምን ከማስጠበቅ አንጻር ደህንነቶቹ ሲረጋገጡ እንደ ሀገር የሚገኙ ዕድሎች አደጋዎቹና የወደፊት ዕይታን በተመለከተ ስለ ጥናቱ ገለፃ ያደረጉ ሲሆኑ የሀገር ሰላምና ደህንነት ሲረጋገጥ የሀገርን ገጽታ ከመገንባት አኳያ ያለው ፋይዳ ምን መምሰል እንዳለበትና ጥናቱም ሲጠና ምን ምን ጉዳዩችን ማካተት እንደሚገባ ጭምር በሰፊው አብራርተዋል።

ጥናቱን ተመርኩዞ በቀረበው ገለፃ ላይ የቢሮው ሀላፊዎቹ ሀሳባቸውን በገለጹበት ወቅት ጥናቱ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያተኮረ እንደመሆኑ መጠን ለሚደረገው ጥናት በበቂ ሁኔታ እውነተኛ መረጃዎችን ከማግኘት አንጻር ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ሀሳባቸውን በመግለጽ ገጽታን መገንባት ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ የቱሪስት የኢኮኖሚ ሴንተር የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጸጥታ ፖሊሲው አስፈላጊ መሆኑ ግዴታም ስለሆነ ጥናቱ በእውነተኛ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመርኩዞ የሚጠና መሆን እንዳለበት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ መድረኩን በመሩት ወቅት እንዳሉት ቢሮው በከተማው ላይ ስለሚያከናውነው የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎችን በበለጠ መልኩ አጠናክሮ ለማስቀጠልና ብሎም የሀገር ሰላም ሲረጋገጥ በሀገር ገጽታ ላይ ያለው ሚና የጎላ እንደመሆኑ በቀጣይ ስራዎቻችንን ስንሰራ ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔዎች ከመሆን አንጻር የጥናቱ አስፈላጊነት አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።