ባለፉት 6ወራት በከተማው ላይ በሰላምና ጸጥታው...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ባለፉት 6ወራት በከተማው ላይ በሰላምና ጸጥታው ለመጣው ውጤት የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ እንደነበር ተገለጸ።

ባለፉት 6ወራት በከተማው ላይ በሰላምና ጸጥታው ለመጣው ውጤት የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ እንደነበር ተገለጸ።

             የካቲት 5/2018 (አ.አ.ሰፀ.አስ.ቢሮ)
                              **
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማው ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በ2018 ዓ.ም በ6ወር  ውስጥ በዕቅድ ይዞ ሲሰራ የቆየውን የዕቅድ አፈጻጸም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ገምግሟል።

በግምገማው መድረክ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ በንግግራቸው ቢሮው ባለፍት 6ወራት ውስጥ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በማቀናጀት የሰላም ባለቤት በማድረግ አዲስ አበባን የሰላም ተምሳሌት በማድረግ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ተመራጭ ከተማ እንድትሆን በመስራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አስታውሰው ለመጣው ውጤትም መላው የከተማውን ነዋሪ  አመስግነዋል።

ከጸጥታው መዋቅር ጋር በመቀናጀት በተለይም ደግሞ ከሸገር ሲቲ ጋር በቅንጅት በትስስር በመሰራቱ በርካታ የአደባባይ በዓላት ሀገር አቀፍና አለማቀፍ ጉባኤዎችና ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው የተካሄዱበት፤ የወንጀል ምጣኔ የቀነሰበት ህብረተሰቡም እንግዶችን ተቀብሎ በሰላም የተሸኘበት የሰላም አደረጃጀቱን መዋቅር ለሰላም ዘብ ሆኖ የቆመበትና በርካታ ስራዎች የተሰሩበት እንደነበርም አብራርተዋል።

ሀላፊው አያይዘውም አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባም የሁሉም መሰረቱ ሰላም በመሆኑ በቀጣይ ሰላሟን በዘላቂነት ለማስቀጠል የህብረተሰቡና የባለ ድርሻ አካሉ ሚና አይተኬ በመሆኑ መንግስት ብቻውን የሚሰራው ስራ ስለማይኖር ከፊታችን በአገር ደረጃ የሚካኔደው 7ተኛው ሃገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ታማኝነት ያለው ሆኖ በሰላም እንዲጠናቀቅና ከሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ አብሮነትን ከሚሸረሽሩ ንግግሮች በመቆጠብ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የቢሮው የጸጥታና መረጃ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው ጽንፈኝነትን በመተው በብዝሀነት የደመቀች ሀገራችንን በኔነት ህሳቤ በመዉጣት በእኛነት ህሳቤ በመራመድ ችግሮችን በንግግር በመፍታት ጸብ ከሚቀሰቅሱ ግጭቶች መራቅ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ሀገር ሰላም እንድትሆን ሰላም የኔ ነዉ ብሎ በማሰብ አዕምሮን ለሰላም በማዘጋጀትና ሰላምን የመፍጠር አስተሳሰብ የኔ ነው ብሎ የሚያስብ ማህበረሰብ በመገንባት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እንዲሰፍን በጋራ መስራት ይገባለ ያሉት አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ ናቸው።
በስድስት ወራት ውስጥ በዕቅድ የተሰሩትን ስራዎች በተመለከተ ገለጻ ያደረጉት አቶ ማስረሻ ሀብቴ የቢሮው የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ዕቅድ ላይ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ከሀላፊዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።