በማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ፣በብሎክ ምልመላ መዛኞች ላይ ግምገማ ተካሄደ።
በማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ፣በብሎክ ምልመላ መዛኞች ላይ ግምገማ ተካሄደ።
የካቲት 05/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ መርሃ ግብር ስር በተመረጡ ብሎኮች ላይ የተካሄደውን የምልመላ መዛኞች ግምገማ ማጠቃለያ ሪፖርት ገመገመ።
የግምገማ ሪፖርቱን ያቀረቡት የየካ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተሬቻ ዳዲ ሲሆኑ በገለጻቸውም፣ግምገማው የተካሄደው ከተማዋን በህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ሰላምና ፀጥታ የሰፈነባት፣ ለመኖር፣ ለስራ እና ለመዝናኛ ተመራጭ የሆነች ከተማ ለማድረግ ያለውን ራዕይ ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።
በግምገማው ሂደት ውስጥ በብሎኮች የታዩ አዎንታዊ ለውጦች፣ ጥንካሬዎችና መስተካከል ያለባቸው ክፍተቶችን በተለይም የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት ጥራት፣ የአባላት ብስለትና የህዝብ ተሳትፎ መጠን በዋናነት ተመልክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር ሙልጌታ በጋሻው በግምገማው ማጠቃለያ እንደተናገሩት ትላንት ከነበረው እንቅስቃሴ በቀጣይ ምልመላውን የበለጠ በማስቀጠል እና ከግምገማው የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ የማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር እና የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ተጨማሪ ግብዓቶች እንደሚወሰዱ ተገልጿል።
በግምገማው ላይ የማዕከል እና የአስራንዱም ክፍለ ከተሞች ዳይሬክተር፣አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።