የቢሮው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬም ቀጥሎ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሮው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

የቢሮው የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል

  የካቲት 6/6/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                       ******
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን  በዛሬው ዕለትም የባለጉዳይ ቀንን አስመልክቶ የቢሮውን አገልግሎት ፈልገው ወደ ተቋሙ ለሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገቢው መንገድ አስፈላጊውን ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል።

የተቀናጀ የአገልግሎት አሰጣጥ በአንድ ማዕከል መኖሩ የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ማግኘት የሚያስችል ሲሆን የተገልጋዩን ማህበረሰብ ጊዜና ጉልበት በመቆጠብ የአገልግሎት አሰጣጡ ፈጣን ግልጸኝነትና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችል ነው።

አግልግሎት በሚሰጥበት ዕለት የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተቋሙን ግልጋሎት ፈልገው ወደ ቢሮ ለሚመጡ የከተማው ነዋሪዎች  ባለጉዳዩችን ተቀብለው በማስተናገድ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

ለማንኛውም ጥቆማና መረጃዎች በነፃ የስልክ መስመራችን በ8882 ያድርሱን በተጨማሪም http ፡//www.aaps.gov.et ዌብሳይታችንን ይጎብኙ