130ኛውን የአድዋ ድል የድል በዓልን አስመልክቶ ከቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።
130ኛውን የአድዋ ድል የድል በዓልን አስመልክቶ ከቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ።
የካቲት 10/6/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ከፊታችን የካቲት 23 "የአድዋ ድል ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል" የሚከበረው 130ኛው የአድዋ ድል በዓልን አስመልክት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በዓሉን አስመልክቶ ለውይይት የሚሆነውን መነሻ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ማስረሻ ሀብቴ ሲሆኑ በዓሉ የመላው የጥቁር ህዝቦች የድል፣ የጽናት፣ የበላይነት የታየበት የሀገር አንድነት በዛ ዘመን ጎልቶ በመውጣት ሀገራችን ኢትዩጵያ ነጻነቷን አስከብራ የምትኖር ሀገር እንድትሆንም አድርጓታል ሲሉ ገልጸው ስለታሪኩ ማስታወሻነቱ ስለ አከባበሩ አጠቃላይ ስለ በዓሉ ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ አብራርተዋል።
ውይይቱን የመሩት አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እንዳሉት የሀገራችንን አደራ ተቀብለን የምንሰራበት ጊዜ ስለሆነ በአንድነት አንድ ሆኖ ድል እንደተሰራ አስታውሰው በሉአላዊነት ውስጥ ያለች ሀገር ስለሆነች ማደግና መበልጸግ ያለብን ሀገሮች ስለሆንን ገናናነትን በማጽናት እሴቶችን ማስቀጠል እንደሚገባና ታሪክን አደራን ተቀብሎ ምን ምን ጉዳዩችን ተግባራዊ አድርገን እየሰራን ነው ብሎ ማሰብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የአድዋ ድል የጥቁር ሕዝቦች ድል፣ የነጻነት እና የአንድነት የታሪክ ድል ሲሆን ዛሬም ይህን ዕሴት በመያዝ ኢትዮጵያን ወደ ማንሰራራት ማምጣት የሁላችን ኃላፊነት በመሆኑ እንደ ተቋም በተሰማራንበት የሞያ ዘርፍ ላይ ሀላፊነትን በመውሰድ
ሕግን በማክበር እና አንድነታችንን በማጠናከር የዘመናችን የአድዋ ድልን በማስቀጠል የአለም ህዝብ በምንሰራው ስራ አይኑን የጣለባት ሀገርም ስላለችን የተሰጠንን ዕድል በመጠቀም የሰላምን ዋጋ በደንብ በመገንዘብ በጋራ ለሰላም መስራትና ቀጣዩን 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በአንድነትና በሰላም እንዲጠናቀቅ በኃላፊነት እንድንወጣ አደራ እላለው ሲሉም አሳስበዋል።
የቀረበውን መነሻ ጹሁፍ መሰረት በማድረግ ከሰራተኞች ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ሀላፊው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።