ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የሰላምና ፀጥታ አመራሮች፣ ዳሬክተሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ስልጠና መስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ።
ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የሰላምና ፀጥታ አመራሮች፣ ዳሬክተሮች፣ አስተባባሪዎች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ስልጠና መስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ።
****
የካቲት 11/2018 (አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ሪፎርም እያደረገ ይገኛል፤ የሪፎርሙ አስኳል ደግሞ ወቅቱን የዋጀ የፀጥታ መዋቅር መፍጠር ነዉ። ከዚህ አኳያ ባለፉት ጊዜያት አመራሩና ሰራተኛዉ በፈተና እንዲያልፍ በማድረግና የአመለካከትና የክህሎት ምዘና በማድረግ ብቁ የሰዉ ሀይል የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፤ እየተሰራም ይገኛል።
የሰራተኛዉ መብት ለማስጠበቅ የBPR ሰነድ በማዘጋጀትና አዲስ የስራ መደብ ጥናት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ተደርጓል፤ ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠርና የፀጥታ ስራዎች በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።
አመራሩና ሰራተኛዉ አመለካከቱ የተስተካከለ የማድረግ አቅሙን ለማሳደግ የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
በዛሬዉ እለትም የስልጠናዉ ቅድመ ዝግጅት ተገምግሟል። ግምገማዉን የመሩት ዶክተር ጀማሉ ጀምበር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ስልጠና ብቁ የሰዉ ሀይል ለመፍጠር እጅግ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ዝግጅቱን በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ሪፎርሙ የተሟላ እንዲሆን የአመራሩና የሰራተኛዉ አስተሳሰብና አቅም ወቅቱን የሚመጥን መሆን እንዳለበት ገልፀዋል፤
ይህንን ለማሳካት ደግሞ የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠና ወሳኝ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዉ ዝግጅቱን በፍጥነት እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የፐ/ሰ/ሰ/ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ የኢትዮዽያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ አመራር የሆኑት ዶ/ር መሳይ እና ኮማንደር ሲሳይ እንዲሁም የተቋሙ የስልጠና አስተባባሪዎች በገለፃው ላይ ተገኝተዋል።