#ኑ_እናገልግሎ!
#ኑ_እናገልግሎ!
የካቲት 11/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንድ ማእከል አገልግሎትን የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማን ጨምሮ የቢሮው ም/ል ኃላፊዎች በተገኙበት ፣ተገልጋዮችን በየሳምንቱ እሮብ እና አርብ እንዲሁም በመደበኛ የስራ ቀናት በቢሮው በመቀበል እያስተናገደ ይገኛል።
ቢሮው ይህን አገልግሎት በማቅረብ የህብረተሰቡን ጥያቄና አስተያየት በቀጥታ ለመስማት፣ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት እና ተገልጋዮች በተቋሙ አገልግሎት ላይ ያላቸውን እርካታ ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ይህ መደበኛ የተገልጋዮች ቀን አስተናጋጅነት የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ እንዲፈቱ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው።
ቢሮው በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መጠናከር እንደሚሰራ አመልክቷል።