በሰላም የመኖር ሂደት ውስጥ የሴቶች ሚና አይተኬ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በሰላም የመኖር ሂደት ውስጥ የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑ ተገለፀ ።

በሰላም የመኖር ሂደት ውስጥ የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑ ተገለፀ ።

******
የካቲት 13/6/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሴቶች ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ከሴት አደረጃጀቶች ጋር በመተባበር "ሴት የሰላም መሰረት፤የልማት አውታር "! በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

በፓናል ውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ባደረጉት ንግግር የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ስራዎች ስፋትና ውስብስብነት እንዲሁም የህዝቡን ፍላጎትና የጸጥታ ስጋት ተጋላጭነትን በመረዳት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ የሚያስችል የሰላምና የጸጥታ ስራዎች በመስራት ሰላም እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ኩል ቢሮው በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ በመጠቆም 

ለሰላም ማጣትና መደፍረስ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ የግጭትና ያለመግባባት አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት መከላከልና መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ሊደርሱ የሚችሉ የጸጥታ ችግሮችን ከማስቀረቱ በተጨማሪ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ መረጋጋት እንዲኖር በማስቻል በኩል የሴቶች አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ መሆኑንም ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል ።

ሴቶች የሰላም መሰረት የልማት አውታር እንደመሆናቸው መጠን በልጆች አስተዳደግና ቤተሰብን በመምራት በስነ ምግባር ኮትኩቶ በማሳደግና ሕግ አክባሪ የሀገር ዜጋ እንዲሆኑ ስብዕናን በመቅረጽ መሰረታዊ አስተዋጽኦ ከማድረግ ጎን ለጎን ቤተሰቦቻቸው ወደ ግጭት ቦታዎች ኤደው እንዳይሳተፉ በማድረገድ በኩል ሚናቸው የጎላ እንደሆነም ጭምር አብራርተዋል።

ለዘላቂ ሰላም ግንባታ በግጭት አፈታትና አስተዳደር እንዲሁም በቀጣይ በከተማው ላይ በሚካኔዱ የሰላም መስፈንና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራዎች ላይ ሴቶች እንደ እናትም እህትም በመሆን ሁሉን አቀፍ ሀላፊነታችሁን በመወጣት በመቻቻልና በመከባበር ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን እሴቶችን እንዲዳብሩ በማድረግ መጭው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ፍትሀዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ በበኩላቸው ልዩነቶችን በውይይትና በሃሳብ የበላይነት እንጂ በግጭት እንዳይፈቱ ማድረግ የሁሉም ዜጎች ተግባርና ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው የሴቶች እና የእናቶች አስተዋፅኦ በማህበረሰብ ውስጥ የሰላም ባህልን ለማጠናከር ቁልፍ መሆኑንም በመገንዘብ ወጣቱ ትውልድ የጥላቻ እና የብጥብጥ መንገድን ሳይመርጥ የፍቅርና የውይይት ባህልን እንዲያበረታታ በማድረግ ረገድ ሴቶች ግንባር ቀደም ሚናቸውን በመወጣት የሰላምን ዋጋ ተረድተው ለከተማውና ለሀገሩ ተቆርቋሪ ዜጋ እንዲሆን የሚሰጠው ምክርና አመራር ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ውስጥ የሴቶች ሚና ምን መምሰል እንዳለበት ገለጻ ከተደረገ በኋላ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣ዶ/ር አቶሜ አበበ የአዲስ አበባ ሴቶች ፊዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የኢፌዴሪ ሴቶች ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ የአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ፣ወ/ሮ የሺ ወልጄ የከንቲባ ሴቶች አደረጃጀት አማካሪ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ሀላፊ በርካታ የከተማው የሴት አደረጃጀት አመራሮች የጉለሌ ክ/ከተማ አስታራቂ እናቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።