8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር መድረክ ላይ የስምምነት ስነ-ስርዓት ፊርማ ተካሄደ።

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር መድረክ ላይ የስምምነት ስነ-ስርዓት ፊርማ ተካሄደ።

የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ ምክክር መድረክ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች እየተመራ የሚገኝ ሲሆን በመድረኩም የፌደራልና የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች፣የሰላም ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች የስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልል ሰላምና ፀጥታ፣የሰላም ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር፣በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ ሥራ ለመስራት በጋራ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

የተፈረመው ስምምነት ቀጣይ በከተማዋ ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የህዝብ ተሳትፎን በማጠናከር፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የደህንነትና የጸጥታ ስራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማስፈፀም የሚያግዝ ነው።

ተሳታፊዎቹ በመድረኩ ላይ የተጀመረው የተቀናጀ የጋራ እንቅስቃሴ የሀገር አቀፍ ሰላምና ጸጥታ ግንባታን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም በተግባር የሚተገበሩ የጋራ እቅዶች እንደሚዘጋጁ አስታውቀዋል።