የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና መሠረት ላይ በመመስረት የላቀ ውጤት ላሳዩ ዘርፎች፣ ዳይሬክተሮችና የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች የእውቅና መርሃ-ግብር አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና መሠረት ላይ በመመስረት የላቀ ውጤት ላሳዩ ዘርፎች፣ ዳይሬክተሮችና የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች የእውቅና መርሃ-ግብር አካሄደ።
የካቲት 26/2018 ዓ.ም (አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
በእውቅና መርሃ-ግብሩ ላይ የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት፣ በዚህ በጀት ዓመት በተለይ የተቋም ግንባታ ዘላቂ እንዲሆንና የተቋማት አደረጃጀት ጠንካራ እንዲሆን ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፣እንዲሁም በዓለም አቀፍ፣ በሀገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ የሚነሱ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ህዝቡን በማደራጀት ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር መስራታቸው የከተማውን ደህንነትና ፀጥታ ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳበረከተ ገልፀዋል።
ይህም የተገኘው ውጤት የሁሉም ተቋማትና ህብረተሰቡ የጋራ ጥረት መሆኑን አመልክተዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የምዘና ሰነዱን ያቀረቡት የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አለምፀሐይ ማሞ ሲሆኑ፣ በምዘናው ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ የተገኙ ግኝቶች፣ የታዩ ደካማ ጎኖች እና የተመዘገቡ ውጤቶች በዝርዝር አቅርበዋል።
በመጨረሻም በ6 ወራት የአፈጻጸም ምዘና ውጤት መሰረት የላቀ ውጤት ላሳዩ ዘርፎች፣ ዳይሬክተሮችና የክፍለ ከተማ ጽ/ቤቶች የእውቅና ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ሲሆን በክ/ከተማ ደረጃ 1ኛ የወጣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፤ 2ኛ አዲስ ከተማ ፤3ኛ ቂርቆስ ክ/ከተማ ሲሆኑ ሌሎችም በቀጣይ በእቅድ አፈፃፀማቸው በርትተው በመስራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባቸው ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ አሳስበዋል።