የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የወንጀ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የወንጀል መከላከል አቅምን ለማጎልበት ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ የወንጀል መከላከል አቅምን ለማጎልበት ሲሰጥ የነበረው   የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።
        **
የካቲት 27/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ፤ስልጠናዉ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣በአካባቢ ህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት ላይ ያተኮረ የወንጀል መከላከልና የስነ-ምግባር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሆነም ተናግረዋል።

የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የወኝጀል መከላከል፣በአጠቃላይ የኃይል ጥቃት ወንጀልና እና የወንጀል ስጋትን ለመቀነስ ከማህበረሰቦች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመስራት እንደሆነም ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የዘርፉ ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻዉ ሲሆኑ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አባላት የከተማዋ የጸጥታ መዋቅር ወሳኝ አካላት መሆናቸዉን አንስተዉ፤ ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት አስቀድሞ መከላከል የሚቻለው አባላቱ የወንጀል መንስኤዎችን በሚገባ ሲረዱና በስነ-ምግባር የታነጸ የጥበቃ ስራ ሲያከናውኑ ነዉ ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለዉም ይህ ስልጠና አባላቱ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት አካባቢያቸውን ከስጋት ነጻ እንዲያደርጉ አቅም ይፈጥርላቸዋል ሲሉ ስልጠናዉን በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል።

በተሰጠው ስልጠና ላይ የወንጀል ምንነት፣ ወንጀልን አስቀድሞ የመከላከል ስልቶች፣ ወንጀል በማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፣ የወንጀል መንስኤዎችና የህግ ማስከበር ግቦች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ቢሮው የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥና የጥበቃ አባላትን የሙያ ስነ-ምግባር ለማሳደግ እየሰራ ካለዉ ተግባር አንድ አካል ነው።