የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የተከለሰ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የተከለሰ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።

የካቲት 27/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የቀሪ ስድስት ወራት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የተከለሰ ዕቅድን ከማዕከልና ከክፍለ ከተማ የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ሰራተኞች ጋር የጋራ አደረገ።

በመድረኩ ላይ የቢሮው የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሃብቴ የተከለሰውን ዕቅድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው እንዳመለከቱት፦

የዕቅድ ክለሳው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን መሰረት በማድረግ፣ ቀሪ ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት ሲሆን ከተማዋ የምታስተናግዳቸውን ታላላቅ ሁነቶችና ነባራዊ የጸጥታ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት፣ ሀብትንና የሰው ኃይልን በቁርጠኝነት ለውጤት ለማሰለፍ እቅዱ ተከልሶ ወደ ተግባር መገባቱ ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ ከማዕከል እስከ 11ዱም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አስተባባሪዎችና የቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። ተሳታፊዎቹም ዕቅዱ በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች ተወርዶ ለውጤት እንዲበቃ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ይህ የተከለሰ ዕቅድ የጋራ መግባቢያ መድረክ፣ ቢሮው የከተማዋን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎች ይበልጥ በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ለማስቀጠል ያለመ ነው።