የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ የህዝቦችን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

 የካቲት  30/2018 ዓ.ም  የአ/አ/ከ/አስ/ሰ/ፀ/ቢሮ
                   
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ   የህዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ፣ እርስ በርስ የመከባበርና የመደጋገፍ እሴቶች የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በስሩ ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር  በጋራ በመሆን  ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ  ተገለፀ።

ዘርፉ ኢትዮጲያዊ አንድነትን የሚያንፀባርቁ  የሀይማኖትና  ሰላም እሴት ግንባታ እንዲሁም ሀገራዊ መግባባትን የሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑ ጠቁመው  ለዚህ ተግባር ውጤታማነት በዘርፉ የሚገኙ ሰራተኞች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ አስገንዝበዋል።

 ዜጎች የሀይማኖትና የሰላም እሴትን ማጠናከር  ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ብሎም የማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ብሎም ለኢኮኖሚያዊ  ዕድገት ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመረዳት ሊጠብቁ እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን   ከተማዋ የአብሮነት ፣ የሀይማኖት ፣ የፍቅርና ፍፁም ሰላም የሰፈነባት እንድትሆን ማድረግ የሰላም ባለቤት ከሆነው  ከነዋሪው  እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችም  በህዝብና በመንግስት የተሰጠን ሀላፊነት  በአግባቡ በመወጣት በዕቅድ የተሰጣቸውን ግብ   የፈጠራና የቴክኖሎጂ ስራዎችን በማከል   ለተሻለ ስኬት  በቁርጠኝነት  መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል።