የመደመር መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት" በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
"የመደመር መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት" በሚል መሪ ሀሳብ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ "የመደመር መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት" በሚል መሪ ቃል፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ጋር ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን መሰረት ያደረገ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የሃይማኖት ተቋማት ሚናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ የመደመር መንግስት የሃይማኖት ተቋማት የሀገርን ሰላም በማፅናትና ልማትን በማፋጠን ረገድ ያላቸውን ሚና በእጅጉ እንደሚያምን ገልጸዋል። መንግስት ለቤተክርስቲያኒቱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱንና ቀሪዎቹም በከተማ አስተዳደሩ አቅም ልክ በሂደት ምላሽ እንደሚያገኙ አረጋግጠዋል።
አክለዉም የሃይማኖት ተቋማት ችግሮች ሲፈጠሩ ችግሮቹን ለመፍታት ተቋማዊ አሰራርን መከተል እንዳለባቸው ኃላፊው አሳስበዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፤ የሃይማኖት ተቋማት የአስተሳሰብ አንድነትንና የጋራ አብሮነትን በማጠናከር ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በስነ-ምግባር የታነጸ ዜጋ በመፍጠርና በልማት ስራዎች ላይ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትልና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ፤ "የመደመር መንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ይህ መድረክ በመንግስትና በ የሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለሀገር ሰላም በጋራ ለመቆም ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል።