የሃይማኖት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
የሃይማኖት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
መጋቢት 2/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የመደመር መንግሥት ለሃይማኖት ተቋማት ያለው ዕይታ በሚል መሪ ሀሳብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የሃይማኖት ተቋማት ለኢትዮጵያ የሀገረ መንግሥት ግንባታና ለሀገራዊ አንድነት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ታላቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ መንግስት ለሁሉም ቤተ እምነቶች እኩል እይታ እንዳለውም ጠቅሰው በተለይም ከለውጡ በሏላ የመደመር መንግስት ከቤተ እምነቶች ጋር ተያይዞ እየሰራ ያለውንም ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ነው ብለዋል።
አቶ ጃንጥራር አያይዘውም በውስጥ አሰራር ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመነጋገርና በውይይት በመፍታት በሀገር ደረጃ የሰላም መደፍረስ እንዳይኖርና የዜጎች ሰላም ማስጠበቅ ይገባል ብለው እኔ ብቻ ከሚል አስተሳሰብ በመላቀቅ አንድነት እንዲጠናከር አበክሮ በመስራት ምህመኑና የአስተምህሮ አባቶች ብዝሀነትን በማሳየት ለአንድ ሀገር በመቆም ለሀገር ግንባታና ለዘላቂ ሰላም በጋራ በመስራት ሀላፊነትን መወጣት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የውይይቱን ዓላማ በመደመር መንግስት ዕይታ ስለ ሀይማኖት ተቋማት አስተዳደራዊ መርሆዎች ስለታሪክ ባለቤትነት ትውልድን ስለመገንባት መርሆዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በተመለከተ በዝርዝር ማብራሪያ ያቀረቡት አቶ ፍስሀ ጥበቡ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብ ምላሽ ተሰቶበታል።
የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሔ አቅጣጫ ይሆናሉ ተብለው ከተቀመጡት ውስጥ በህግ መመራት፣ተቋማዊ አንድነትን ማጠናከር፣ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ መስራት፣ጽንፈኝነትና አክራሪነትን መቃወም፣በማህበራዊ ልማት ላይ መሳተፍ፣ፖለቲካና ሀይማኖት መለየት፣ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት የሚሉት ተጠቅሰዋል።
ውይይቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ11ዱም ክ/ከተሞች ተካሂዷል።
ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከታተሉ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
ዌብሳይት ገፅ :- https://www.aaps.gov.et/
የቲክቶክ ገፅ:- http://tiktok.com/@user66126004397614
የፌስ ቡክ ገፅ:- https://web.facebook.