የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ "የመደመር መንግሥት እይታ በሀይማኖት ተቋማት በሚል መርህ ከወንጌላውያን አማኞች የሀይማኖት አባቶች ጋር በ11ዱም ክ/ከተሞች ውይይት አካሄደ።
የሀይማኖት ተቋማት የስነ-ምግባርና የሰላም እሴቶችን ለትውልዱ በማስረፅ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የድርሻቸውን እዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
መጋቢት 3/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ "የመደመር መንግሥት እይታ በሀይማኖት ተቋማት በሚል መርህ ከወንጌላውያን አማኞች የሀይማኖት አባቶች ጋር በ11ዱም ክ/ከተሞች ውይይት አካሄደ።
አቶ ጥላሁን ወርቁ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ በንግግራቸው በኢትዮጵያ ምድር ላይ የሀይማኖት አባቶች ለሀገረ መንግሥት፣ ለትውልድና ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ሀላፊነትን በመውሰድ ሀላፊነታቸን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ሀላፊው አክለውም የሀይማኖት ተቋማት በሀገረ መንግስት ግንባታና በመደመር መንግስት አሁናዊ እይታ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸውና ትውልድን በመቅረጽ በማስተማር አስተምህሮው በሚያዘው መንፈሳዊ አለም የሚመራ ትውልዱ ፈርሐ እ/ር እንዲኖረው በስነ ምግባር በባህል እሴት በማነጽ ብልሹ አሰራርን በማረም ሀገሩን፣ቤተሰቡን ብሎም እራሱንና ማህበረሰቡን በመውደድ ቅን ልቦና እንዲኖረው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ።
መንግስት ለሁሉም ቤተ እምነቶችና የእምነት ተቋማት በእኩልና በተመሳሳይ ሁኔታ በማስተናገድ በሀገራዊ የልማት ስራዎች ውስጥ እንደሚሳተፉና በተለይ ደግሞ ከለውጡ በኋላ በሁሉም ቤተ እምነቶችና ተቋማት ላይ ትኩረት በመስጠት በነፃነት በሀገር ግንባታ ላይ ሀላፊነታቸውን በበለጠ በመወጣት ተቀናጅቶ በመስራት በሀገር ሰላም ጥበቃ ላይም ሀላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም አብራርተዋል።
አቶ ጥላሁን አክለውም የሀይማኖት ተቋማት የተቋቋሙለትን ዓላማ በአግባቡ ከተወጡ ለሀገር ዕድገት ለሰላም አሰተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በእኔነት እሳቤ በጋራ በመስራት ሰላምን ከትውልድ ትውልድ በማስተላለፍ የሃገርና የከተማን ሰላም ማስጠበቅ ይጠበቅብናል አሳስበዋል።
ዶ/ር ምስክር ነጋሽ የቂርቆስ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ለሀገረ መንግስት ግንባታ የማይተካ ጉልህ ዘመን ተሻጋሪ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳላችሁ የሀይማኖት አባቶች የሚታወቅ ሲሆን ሚናውም ከፍተኛ በመሆኑ በብዙ ምክንያት ሲገፋ የኖረ ህዝብን እኩልነት ያረጋገጠ የእምነት ነጻነትን አክብሮ ያስከበረ ዕንባ ያበሰ የለውጡ መንግስት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለሰው ልጆች እኩል ዕድልን እየሰጠም በመገኝቱ በቀጣይም በጋራ በመግባባት የማንፈታው ችግር አይኖርም ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።
የውይይቱን ዓላማ መሰረት ያደረገው ስለ መደመር መንግስት ዕይታ ስለ ሀይማኖት ተቋማት አስተዳደራዊ መርሆዎች አንድነትን ስለማስጠበቅ ጽንፈኝነትንና አክራሪነትን መከላከል በቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እና ህጋዊነት ቦታዎችን ስለማስከበር ስለ አምልኮ ስርዓቱን ስለታሪክ ባለቤትነት ትውልድን ስለመገንባት ሀገረዊ ተሳትፊን ስለማረጋገጥ መርሆዎችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በተመለከተ በዝርዝር ማብራሪያ ያቀረቡት አቶ ፍስሀ ጥበቡ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ለተነሳው ሀሳብ ምላሽ ተሰቶበታል።
የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የመፍትሔ አቅጣጫ ይሆናሉ ተብለው ከተቀመጡት ውስጥ በህግ መመራት፣ተቋማዊ አንድነትን ማጠናከር፣ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ መስራት፣ጽንፈኝነትና አክራሪነትን መቃወም፣በማህበራዊ ልማት ላይ መሳተፍ፣ፖለቲካና ሀይማኖት መለየት፣ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት የሚሉት ተጠቅሰዋል።
ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከታተሉ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
ዌብሳይት ገፅ :- https://www.aaps.gov.et/
የቲክቶክ ገፅ:- http://tiktok.com/@user66126004397614
የፌስ ቡክ ገፅ:- https://web.facebook