የመንግስት አገልግሎት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የመንግስት አገልግሎት ውጤታማነት ለማረጋገጥ የጋራ ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ።

የመንግስት አገልግሎት ውጤታማነት ለማረጋገጥ  የጋራ ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ።

       መጋቢት 03/ 07/2018 ዓ.ም 
              *አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.ቢ*

የመንግስት አገልግሎት ውጤታማነትን ለማሳደግ በተቋማትና በተገልጋዮች መካከል የጋራ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከ11ንዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ የተገልጋይ መማክርት ምክር ቤት አባላት ጋር በመድረክ በመገናኘት የአገልግሎት አሰጣጥ ፅንሰ–ሀሳብ፣ መሠረታዊ ባህሪያት እና ለብልሹ ተጋላጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል።

የቢሮው አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ በቢሮው የሚሰጡ አገልግሎቶች ህዝቡ ጋር እንዲደርሱና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ  እንዲቻል ብሎም በተቋሙ  ውስጥ ለውጥ እንዲያመጣ በትኩረት  መስራት እንደሚገባ  ገልፀዋል።

በተጨማሪም የአመለካከት ለውጥ በመፍጠር በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚታዩ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምጸሐይ ማሞ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ የውይይቱ ዋና ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚያቀርቡትን አገልግሎት በተደራጀ እና ውጤታማ አሰራር እንዲመሩ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

እንዲሁም ተቋማቱ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ እንዲችሉ ማገዝ የውይይቱ ተጨማሪ ዓላማ መሆኑን አብራርተዋል።
በውይይቱ ተሳታፊዎችም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የሚታዩ ችግሮችና ለብልሹ ተጋላጭ የሆኑ ጉዳዮችን በመግለጽ ለመፍትሄው የሚረዱ አስተያየቶችና ሀሳቦችን አቀርበዋል።

መድረኩ በመንግስታዊ ተቋማትና በተገልጋዮች መካከል የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑም ተመላክቷል።

ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችንን ይከታተሉ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

ዌብሳይት ገፅ :-  https://www.aaps.gov.et/

የቲክቶክ ገፅ:-  http://tiktok.com/@user66126004397614

የፌስ ቡክ ገፅ:-  https://web.facebook.