የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውጤታማ አፈፃፀም ማሳየቱ ተገለፀ።
የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በተያዘው በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውጤታማ አፈፃፀም ማሳየቱ ተገለፀ።
መጋቢት 04/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት አመት ባለፉት ስምንት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍስሐ ጥበቡ በተገኙበት ከ11ዱም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ጋር በዝርዝር ገምግሟል።
በመድረኩም ባለፉት ስምንት ወራት በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የዘርፉ ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ተነስቶ፤በከተማዋ በርካታ ታላላቅ ሀገራዊና አህጉራዊ ኩነቶችን በስኬት አስተናግዳ ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቃቸው፤ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከህብረተሰቡ ጋር ምን ያህል ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን በተግባር የታዩባቸው ስኬቶች ተዳሷል።
አቶ ፍስሃ ጥበቡ የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በመድረኩን በመሩበት ወቅት እንደገለጹት ስራው በሪፖርት ብቻ ሳይሆን በከተማዋ በታየው መረጋጋትና ነዋሪው በሰላም ወጥቶ በመግባቱ ሊለካ እንደሚገባ ገልጸው፤ በቀሪ ወራት ይህንን ስኬት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የከተማዋን ሰላም ይበልጥ ዘላቂ ለማድረግ በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።
የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻዉ በበኩላቸው ለዘርፉ ስኬት መስካት የባለሙያዎችን ሚና የሚበረታታና ሊቀጥል የሚገባው መሆኑን ገልፀው ይህ ውጤት በህዝብ እርካታ የተረጋገጠ ነው ብለዋል። አያይዘውም ያለውን ጥንካሬ በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን በማረም በእዉነት ላይ የተመረኮዘ ጭብጥ በመያዝ ከሌሎች አደረጃጀት ጋርም ተሳስሮ የሰላም ግንባታ ሂደቱን ማጠናከር ይገባልም ነዉ ያሉት።
በመድረኩ የቀረበው የስምንት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፤ በየክፍለ ከተማው የሰላም ሰራዊት ግንባታ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች እና የወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ የታዩ ጥንካሬዎችንና በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸውን ክፍተቶች በዝርዝር ዳስሷል።
ባለሙያዎቹና የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች በስራ ሂደት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች ያቀረቡ ሲሆን፣ ከአመራሩ ጋር በጋራ መፍትሄዎች ላይ መግባባት ተደርሷል።
በመጨረሻም፣ የተገኘው ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በቀጣይ ለሚከናወኑ ታላላቅ ሀገራዊ ስራዎች የጸጥታ መዋቅሩና የህዝብ አደረጃጀቱ ስራ ተቆጥሮ በተሠጠዉ ልክና በተቀመጠዉ ግብ በንቃት እንዲሳተፉ ተመላክቶ መድረኩ ተጠናቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
ዌብሳይት ገፅ :- https://www.aaps.gov.et/
የቲክቶክ ገፅ:- http://tiktok.com/@user66126004397614
የፌስ ቡክ ገፅ:- https://www.facebook.com/share/189aS6cL13/
ቴሌግራም - https://t.me/testchannel578845