1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲዉል ከመጅሊስ አመራሮችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
የ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲዉል ከመጅሊስ አመራሮችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
መጋቢት 7/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀይማኖታዊና ብሔራዊ ክብረ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉ በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ የሚታወቅ ሲሆን መጭው 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲውል ከመጅሊስ አመራሮችና ከበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በበኩላቸው በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅርና የመረዳዳት መሆኑን ጠቁመው ይህን ድባብ በማስጠበቅ ሀይማኖታዊ እሴቱን ሳይለቅ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ወንድማማችነትና እህትማማችነት አብሮነት በተሞላበት መንገድ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩና እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ ገልጸዋል ።
ከአሁን ቀደም ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በጋራ በመወያየት የአደባባይ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ ሆነው መጠናቀቃቸው የአብሮነት እሴት ማሳያ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ መንግስትና የሀይማኖት ተቋማት በሰላም ዙሪያ በቅንጅት በመሰራቱ የሀይማኖት ተቋማት የሰላም መገንቢያ በመሆናቸው ለከተማው ተጨማሪ አቅም መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊነትንና ወንድማማችነትን በሚያስተሳስር ትህትና ፍቅርን አብሮነት በሚያሳይ መልኩ መከበር እንደሚገባው በማስገንዘብ ለጋራ ደህንነት ሲባል ለሰላም ዘብ ሆኖ መቆም እንደሚገባው ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ ተናግረዋል ።
የሀይማኖቱ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በሰላም አክብሮ እንዲውል ከባለፍት አመታት በተሻለ መልኩ በማክበር በሰላም ወጥቶ በሰላም በመግባት የሀገርን ገጽታ የምናሳይበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከሀይማኖት አባቶችና ከመንግሥት የጸጥታ አካላት የሚተላለፈውን መልዕክት አክብሮ በዓሉ በሰላም እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
ዌብሳይት ገፅ :- https://www.aaps.gov.et/
የቲክቶክ ገፅ:- http://tiktok.com/@user66126004397614
የፌስ ቡክ ገፅ :- https://www.facebook.com/share/189aS6cL13/
ቴሌግራም - https://t.me/testchannel578845
ዮቲዮብ:- https://youtube.com/@addisababapeacesecuritybureau?si=fwScl54k_vwpqqji