ወጣቶች ለከተማው ዕድገትና ብልጽግና በጋራ በመሆ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ወጣቶች ለከተማው ዕድገትና ብልጽግና በጋራ በመሆን ህብረ ብሔራዊነትንና አብሮነትን በማጠናከር የሰላም ዘብ መሆን እንደሚገባቸው ተገለፀ ።

ወጣቶች ለከተማው ዕድገትና ብልጽግና በጋራ በመሆን ህብረ ብሔራዊነትንና አብሮነትን በማጠናከር የሰላም ዘብ መሆን እንደሚገባቸው ተገለፀ ።

    መጋቢት 9/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖትና ሰላም እሴት ግንባር ዘርፍ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ወጣቱ ትውልድ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመቃወም ሀገር ግንባታ ላይ በመሳተፍ  በከተማው ውስጥ በሚፈጠሩ አደረጃጀቶችና ዘርፈ ብዙ ጉዳዩች ላይ በመሳተፍ ለከተማው ዕድገትና ብልጽግና በጋራ በመሆን ህብረ ብሔራዊነትንና አብሮነትን በማጠናከር ለሰላም ዘብ መሆን ይገባቸዋል በማለት ከወጣቶች ጋር ምክክር አድርጓል ።

በምክክሩ ላይ አቶ ገብሬ ዳኝው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በንግግራቸው ሀገራችን የምትገነባው ስርዓት ብዝሀነትና አካታችነትን ያማከለ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሰፈነባት እንደመሆኗ  ከዚህ በጨማሪም   በተፈጥሮ መስህብ የለመለመች ስለሆነች በልማቱ በመሳተፍ ከድህነት  በመውጣት ለሰላም መሰረት የሆነውን አንድነትን በማጠናከር ብዝሀነትን ማሳየት እንደሚገባ የቢሮው አማካሪ ገልፀው። 

የልማት ስትራቴጂን በመለማመድ ከኔነት እሳቤ በመውጣት ወደ እኛነት አመለካከት በማምጣት የሰው ልጆችን ሰላም በማረጋገጥና የሰላሙ ዘብ በመሆን ለሀገር በመቆርቆር ቅንጅታዊ ስራዎችን በማከናወን  ሂደት ውስጥ አዲስ አበባ ሰላም ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ሀገራዊ አለማቀፍዊና አህጉራዊ ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው መከናወናቸውን አውስተው አካባቢዎች ላይ የሚያጋጥሙ  ችግሮችን በውይይት የሚፈታ በዲሞክራሲ ስርዓት የሚያምን ወጣት በመፍጠር በቀጣይ በሀገረ አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ምርጫ በመሳተፍ ሀላፊነታቸሁን እንድትወጡ በማለት አቶ ገብሬ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ወጣት በረከት ቢርቢሳ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፕሬዝደነት በበኩላቸው የሰላሙ ባለቤት ወጣቱ እንደመሆኑ መጠን ሰላምን ለማስፈንና ለመጠበቅ በጋራ በመስራት ወጣቶች የሀገር ባለቤት እንደመሆናቸው መጠን  ሀገር የሚጠብቅብንን ሀላፊነትና ግዴታ በመወጣት ልማት እንዲቀጥል ሰላም እንዲረጋገጥ በጋራ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አቶ አብዲ አማን የኢትዮጵያ ሰላም ልማትና ብልጽግና ድርጅት ፕሬዝደንት በመድረኩ በመገኝት ከተማዋ ሁሉም ማህበረሰብ በእኩልነት የሚኖርባት የዲፕሎማሲ ከተማ ሀገርን በመልካም ጎን በማስተዋወቅ በኩል ወጣቱ ትውልድ ሞዴል ሆኖ ህብረ ብሔራዊነትን በማረጋገጥ በዕውቀት የታነጸ በበላይነት የሚያምን ፈጣን በሀገሩ የሚኮራ ስለ ሰላም የሚሰብክ ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ህብረ ብሔራዊነታችን ለአብሮነቻችንና ለሰላማችን በሚል መሪ ቃል በአቶ ሙሉቀን እንየው የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አማካኝነት ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79