ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በተቋማ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በተቋማዊ ጥረት ብቻ ሳይሆን በህዝባዊ ተሳትፎ ሊደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ።

ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በተቋማዊ ጥረት ብቻ ሳይሆን በህዝባዊ ተሳትፎ ሊደገፍ እንደሚገባ ተገለጸ። 
          ***
መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት፤ በብልሹ አሰራርና በሙስና መከላከል እንዲሁም ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥን በማረጋገጥ ዙሪያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በስልጠና መድረኩ ላይ ከ113ቱም ወረዳዎች የተወጣጡ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የተለያዩ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች የተሳተፉ ሲሆን፣ ዓላማውም ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ህዝቡ የበኩሉን የቁጥጥርና የባለቤትነት ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ነው።

ስልጠናውን የሰጡት የቢሮው የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰላም አምሳሉ ስልጠናዉን በሠጡበት ወቅት  እንደገለፁት፤ሙስና እና ብልሹ አሰራር የከተማችንን ሰላምና የህዝባችንን ተጠቃሚነት የሚገዳደሩ ዋነኛ ጠላቶች ናቸው ያሉ ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ግልጽነትና ፍትሃዊነት እንዲሰፍን ሁሉም የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች ብልሹ አሰራርን 'አይሆንም!' በማለትና ጥቆማዎችን በመስጠት ግንባር ቀደም ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባልም ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለዉም  ምቹ የስራ አከባቢን በመፍጠር በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውንም አይነት የሙስና አዝማሚያ ሲስተዋል  የማይታገስና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የስነ ምግባር መመሪያዎች በየተቋማቱ እንዲተገብሩ በመምከር ለዚህም ስኬት የህዝብ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።

በመድረኩ ላይ ሙስና በሀገር ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ መርሆዎች እና የዜጎች የመጠየቅ መብት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ተሳታፊዎቹም በየወረዳቸው የሚያጋጥሙ የብልሹ አሰራር ስጋቶችን በጥያቄና አስተያየት መልክ በማንሳት የጸረ ሙስና መግቻ ስልቶችን ምክረ ሀሳብ ሰጥተዉ፣ በቀጣይ ህግን በማስፈጸም ሙስናን ለመከላከል ከመንግስት ጋር በቅንጅት ለመስራት ቃል ገብተዋል።

ይህ ስልጠና መንግስት የህዝብ አመኔታን ለመጨመር፣ሙስናን የሚጸየፍ ትዉልድ እንዲኖር በማድረግ በንጹህ የስነ-ምግባር መርህ የሚመራ አሰራርን በመገንባት የአገልግሎት አሰጣጥንን ለማሳለጥ ለጀመረው ጉዞ ትልቅ ግብዓት የሚሆን መሆኑም ተመላክቷል።

#አዲስ_አበባ #ሰላምና_ጸጥታ #ጸረ_ሙስና #ግልጽነት #የህዝብ_ተሳትፎ #AddisAbaba #EthicsAndAntiCorruption #Transparency

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79