የከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተካሄደውን 8ኛው ሀገራዊ የሰላምና ፀጥታ የጋራ ምክክር መድረክ አፈጻጸም ገምግሟል።
የከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተካሄደውን 8ኛው ሀገራዊ የሰላምና ፀጥታ የጋራ ምክክር መድረክ አፈጻጸም ገምግሟል።
መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
በ8ኛው ሀገራዊ የሰላምና ፀጥታ የጋራ ምክክር መድረክ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት የመድረኩ ዓላማዎች፣ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች፣ በውይይቱ የተነሱ ቁልፍ ጉዳዮች እና የተገኙ ውጤቶችን የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስተር የፌደራሊዝምና የመንግስታት ግንኙነት መሪ ስራ አሰፈጻሚ የሆኑት አቶ ግርማ ቸሩ በዝርዝር አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ተሳታፊዎች በከተማው አንዳንድ ቦታዎች በመዘዋወር ተሞክሮ መለዋወጥ ሲያደርጉ ከሌሎች ክልሎች የመጡ ተሳታፊዎች መነሳሳት ከመፍጠሩ ባሻገር፣የሰላምና ፀጥታ ተቋማት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያላቸው ሚና እንዲገነዘቡ መደረጉ እና ለወደፊት የሚወሰዱ ትምህርቶችም በጥንካሬና በድክመት ተገምግመዋል።
በመድረኩ ላይ አወያዮች እንደገለጹት፣ በከተማዋ የሚካሄዱ የፀጥታና የማህበረሰብ ልማት ስራዎች በተቀናጀ መልኩ ሲፈፀሙ ውጤታማነታቸው እንደሚጨምር ተጠቁመው፣በተለይም ከተለያዩ ተቋማትና አደረጃጀቶች ጋር የሚካሄዱ ስራዎች በግልፅ ሰነዶች ተዘጋጅተው ወደ ክልሎች መውሰድና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
እንዲሁም የመድረኩ ተሳታፊዎች የማህበረሰብ ተሳትፎ በፀጥታና በልማት ጉዳዮች ላይ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም፣ ተቋማት በመቀናጀት እና በመረጃ መጋራት በቀጣይ ዘመን የሚሰሩ ስራዎችን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
በአጠቃላይ መድረኩም የተጀመሩ የቅንጅት ስራዎችን በማጠናከር የጋራ ኃላፊነት መውሰድ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79