ህገወጥነትን በመግታትና የገበያ መረጋጋትን በማረ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ህገወጥነትን በመግታትና የገበያ መረጋጋትን በማረጋገጥ የከተማዋን ነዋሪ ምቹ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖረውና ከተማዋ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማነቷን የማስቀጠል ስራ በተጠናከረ ስምሪት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ህገወጥነትን በመግታትና የገበያ መረጋጋትን በማረጋገጥ የከተማዋን ነዋሪ ምቹ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖረውና ከተማዋ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማነቷን የማስቀጠል ስራ በተጠናከረ ስምሪት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ። 
           ***
መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ጸ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ፤ ባለፉት አራት ወራት ከ15 ቀናት የተከናወኑ መጠነ ሰፊ የቁጥጥርና የህግ ማስከበር ተግባራትን ከጠቅላላው የጋራ ግብረ-ኃይል ጋር በዝርዝር በገመገመበት ወቅት   ህገወጥነትን በመግታትና የገበያ መረጋጋትን በማረጋገጥ የከተማዋን ነዋሪ ምቹ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖረውና ከተማዋ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማነቷን የማስቀጠል ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። 

በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊና የንዑስ ኮሚቴው  ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣  የከተማ አስተዳደሩ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ እንዲሁም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የጸጥታ፣ የደንብ ማስከበር፣ የገቢዎችና የትራፊክ ማስተባበሪያ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊና የንዑስ ኮሚቴው ሰብሳቢ  መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደገለጹት ላለፉት ሶስት አመታት ህገወጥ ስርዓትን በመቆጣጠር የህግ የበላይነትን ለማስፈን ንዑስ ኮሚቴዉ አመርቂ ዉጤቶችን ማሳየቱን ጠቅሰዉ፤ህጋዊነትን ማስፈን ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አበክረዉ በማዉሳት፤ በከተማዋ 5ቱ የኬላ በሮች ላይ የሚደረገው የመጋዘን ፍተሻ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ስጋት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም፣ ነዳጅ በመደበቅና በማከማቸት በህብረተሰቡ ላይ ችግር የሚፈጥሩ አካላትን መታገስ እንደማይገባ አመላክተዋል። 

ሀላፊዋ አክለዉም በከተማዋ ያሉ የነዳጅ ማደያዎች 24 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡና ህገወጥ ስርጭት እንዲቆም የጸጥታ መዋቅሩ በቁርጠኝነትና ከሌብነት በጸዳ መልኩ ሊንቀሳቀስ ይገባል ብለው ከአሰራር የሚወጡ ነጋዴዎች ከስህተታቸው ታርመው ወደ ትክክለኛ የአሰራር ሂደት እንዲገቡ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወ/ሮ   ሀቢባ ሲራጅ  የአዲስ አበባ የንግድ ቢሮ ኃላፊ  እንዳሉት የገበያ መረጋጋትን ለማረጋገጥ በቂ ምርት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ሲሆን እንደሆነ በማንሳት  በተለይም ምርት በሚደብቁና የሚያከማቹ  ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ  ህዝቡ  ጋር በአግባቡ  እንዲደርሱ ማስቻል እንደሚገባ በማመላከት  ከዋጋ በላይ የሚሸጡና የንግድ ስርዓቱን የሚያናጉ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ  መውሰድ  እንደሚገባ አስገንዝበዋል።  ኃላፊዋ አክለውም  የንግድ ስርአቱ በምሽትም ቀጣይንነት   እንዲኖረው በተቀመጠው  አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊነቱ ላይ ወጥነት የማይታይበት በመሆኑ  በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲገቡ አፅንኦት ሰጥተው  በየደረጃው ያለው የክትትል ሰንሰለትን በማጥበቅ ለነዋሪው እረፍት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ም/ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  ም/ጠቅላይ አዛዥ በበኩላቸው  በንግድ  ስራ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ አልተገባ ስርአት እንዳይገቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው  ከአሰራር የሚወጡ ነጋዴዎችን አሰራርን በጠበቀ መልኩ  ወንጀልን መከላከልና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበው ከዚሁ  ጎን ለጎን የኢኮኖሚ አሻጥርን የሚያራምዱ ከገበያ ማዕከላት እስከ መደበኛ ግብይት ድረስ ያለውን ሰንሰለት በመቆጣጠር፣ በዋጋ ተመን ላይ የሚደረጉ ህገወጥ ጭማሪዎችን ማስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል።  

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም  የመንገድ ላይ ካሜራዎች (cctv)  ተግባራዊ ማድረግና የትራፊክና የጸጥታ መዋቅሩ በቅንጅት በመስራት፣ ከተማዋ ያለምንም የጸጥታ ስጋት የንግድ እንቅስቃሴዋ  እንዲቀጥል ብሎም ከነዳጅ ጋር በተፈጠረው የአቅርቦት ማነስ በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆንና ኃላፊነትን በአግባቡ  መወጣት  እንደሚገባም አሳስበዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ባቀረቡት ሰነድ፤ ግብረ-ኃይሉ በከተማዋ የንግድ ሥርዓቱን ለማሳለጥና ህገወጥነትን ለመከላከል ያከናወናቸውን ስራዎች ዳስሰዋል። በኬላዎችና በመጋዘኖች ላይ የተደረጉ ፍተሻዎች፣ በዋጋ ተመን ላይ የተደረገ ቁጥጥር እና ህገወጥ የነዳጅ ዝውውርን የመግታት ስራዎች በጥንካሬ የተነሱ ሲሆን፤ በተግዳሮት በኩል ደግሞ ከሌብነትና ከቁርጠኝነት ማነስ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ክፍተቶች በግልጽ ቀርበዋል።

በመጨረሻም  ንዑስ ኮሚቴው  በኬላዎች ላይ የሚደረገውን ፍተሻ ይበልጥ እንዲያጠናክር፣ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግና 24 ሰአት ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ ፣ በኑሮ ውድነት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ህገወጥ ደላሎችና ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንዲሁም  ከፊታችን የሚከበረው የፋሲካ በአል ጋር በተያያዘም  የዋጋ ጭማሬና የምርት አቅርቦት ማነስ  እንዳይፈጠር እንዲሁም የንግድ ስርአቱ ከደላላ ነፃ የሆነ የግብይት ስርአት እንዲኖር ግብረሀይሉ  በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ  አቅጣጫ ተቀምጦ ውይይቱ ተጠናቋል።

#አዲስ_አበባ #ሰላምና_ጸጥታ #ህግ_ማስከበር #የገበያ_መረጋጋት #ነዳጅ_ቁጥጥር 
        https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79