የከተማዋን የፀጥታና የደህንነት ሁኔታ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግባራዊ መደረጉ በከፍተኛ ሁኔታ የወንጀል ድርጊት እንዲቀንስ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
የከተማዋን የፀጥታና የደህንነት ሁኔታ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግባራዊ መደረጉ በከፍተኛ ሁኔታ የወንጀል ድርጊት እንዲቀንስ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
መጋቢት 19/2018 ዓ.ም (አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ የውስጥ ለውስጥ ፖልና የመንገድ መብራት ማስበራት ግብረ ሀይል በልደታ ክ/ከተማ በሶስት ወረዳዎች የተከናወኑ የውስጥ ለውስጥ የመብራት ማስበራት ፣ የደህንነት ካሜራዎች ያለውን አፈፃፀምና ሞዴል የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን በምልከታውም ከዚህ በፊት የነበሩ አስቸጋሪና ለወንጀል ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገምገሟል።
በተቀናጀ የሞዴል ብሎኮች የፈጠራ ስራ ከኮሪደር ልማት ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም የፀጥታ ጥበቃውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ብሎኮች ፅዱ ፣ውብና ለነዋሪዎች ምቹ መኖሪያ መፍጠር መቻሉ በግምገማ መድረኩ ተመላክቷል ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የግብረሀይሉ ሰብሳቢ እንዳሉት አዲስ አበባ የዲፕሎማት ከተማና በርካታ ሀገራዊ የኢኮኖሚና ፣ የማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች የሚከናወንባት እንደመሆኗ ሰላሟ የተረጋገጠባት ምቹና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ እንድትሆን በሁሉም ክ/ከተሞች የሞዴል ብሎክ ስራ በትኩረት በመሰራቱና የፀጥታና የደህንነት ጥበቃን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተግባራዊነትን ማስፋት በመቻሉ ሰላሟ የተረጋገጠባት እንድትሆን አስችለናል ብለዋል።
ኃላፊዋ አክለውም አሁን ላይ ያለውን ዘላቂ ሰላም ለማስቀጠል የፀጥታ መዋቅሩ ከህብረተሰቡና ከሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ጋር በጋራ በመሆን በክ/ከተሞች ላይ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠርና በደህንነት ካሜራዎች በመታገዝ ወንጀልን መከላከልና ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማነቷን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለበት በማህበረሰቡ ተሳትፎ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጥበት የውስጥ ለውስጥና የመንገድ መብራትና ሞዴል ብሎክ ስራዎች በክ/ከተማው በውጤታማነት ማከናወን መቻሉን አንስተው በዚህም ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባና የወንጀልን ድርጊት መቀነስ መቻሉን አብራርተዋል።
የግብረሀይሉ አባላትም በምልከታው ማጠቃለያ ላይ እንዳሉት የፀጥታና የደህንነት ሁኔታዎችን በቴክኖሎጂ በታገዘና ሞዴል ብሎኮችን የማፍራት ስራ የከተማችን ነዋሪዎችም ሆኑ ወደ ከተማችን የሚመጡ እንግዶች ግብይትንም ጉብኝትንም በሰላማዊ ሁኔታ ማከናወን እንዲችሉ ማድረግ እንደተቻለ ገልፀው ለዚህም መንግስት ከህዝብ ጋር በጋራ መስራት በመቻሉ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በመጨረሻም ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፣ አፈፃፀምን መሰረት ያደረገ የዕቅድ ክለሳ ፣ ሲሲቲቪ ካሜራ በሁሉም ብሎኮች እንዲገጠሙ ማድረግ ፣ ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጫ መገንባትና አገልግሎት ማስጀመር ፣ የመሰረተ ልማት ሀብትን ማስጠበቅ ላይ ግብረሀይሉ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ተመላክቷል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79