የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለአዳማ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለአዳማ ከተማ አቻው ልምድ አካፈለ።
መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
(የአ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የማህበረሰብን ሰላም ለማረጋገጥና የህግ የበላይነትን ለማስፈን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በርካታ ስራዎችን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። ይህን የህዝብንና የሀገርን ደህንነት በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ የሰራቸውንና እየሰራበት ያለውን ልምድ ለአዳማ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች አካፍሏል።
ቢሮው በአራት ዘርፎች ከሚሰጣቸው 9 አገልግሎቶች 7ቱ በቴክኖሎጂ የሚሰጡ መሆናቸውንና የተገኙ ውጤቶችን ፣ 24 ሰአት ከህብረተሰቡ በኦንላይን ከፀጥታ መረጃ ጋር በተያያዘ ጥቆማ የሚቀበልበት ፣ ከህዝብ አደረጃጀት ጋር የሚሰራበትን አግባብ ፣ ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅርበትና በቅንጅት የሚሰራበትን ሂደት ፣ ከሀይማኖትና ከሰላም ዕሴት ግንባታ አንፃር ፣ ከኦፕሬሽን ፣ ከፀጥታ ደህንነት ስራዎች አኳያ ፣ ከህዝብ አደረጃጀትና ከመረጃ ተደራሽነት አንፃር የሚሰራበትን አግባብ በመረጃ የተደገፈ ልምድ አካፍሏል።
የቢሮው አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ ህዝቡ የፀጥታ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን አምኖ የሰላም ባለቤት በመሆን ለከተማ ዕድገትም ሆነ ለህብረተሰቡ ሰላም መረጋገጥ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀው ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፀጥታ መዋቅሩና የህዝብ አደረጃጀቶች የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመው ለቢሮው ውጤታማነት የአመራሩና የሰራተኛው በትጋትና በቅንጅት የመስራት ውጤት መሆኑን አብራርተዋል።
አቶ ጌታሁን አክለውም በቢሮው መደበኛ የሆነ የስራ ክፍፍልና ስምሪት የሚሰጥና በቁርጠኝነትና በቅንጅት ተግባራት የሚከናወንበት ተቋም ነው ብለዋል።
የአዳማ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ተስፍዬ በቢሮው ያገኙት ልምድ ጥሩ አቅምን የሚፈጥር መሆኑን አንስተው በተለይም አዲስ አበባ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚኖርባትና የዲፕሎማቶች መቀመጫ እንደመሆኗ ያለምንም የፀጥታ ችግር ሁነቶች መከናወናቸውና ሰላሟ የተረጋገጠባት መሆኗ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን አግባብ ይመሰክራል ብለው ያገኙትን ልምድ በማስፋት እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል።
የልምድ ልውውጦች ለላቀ ውጤታማነት !!
ለወቅታዊ መረጃዎች :-
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79