"ህብረብሄራዊነታችን ለአብሮነታችንና ለሰላማችን"
"ህብረብሄራዊነታችን ለአብሮነታችንና ለሰላማችን"
መጋቢት 2018 ዓ.ም ( አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ/
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ "ህብረብሄራዊነታችን ለአብሮነታችንና ለሰላማችን" በሚል መሪ ቃል ከሸገር ሲቲ አጎራባች ክ/ከተሞች ጋር ሲያካሂድ የነበረውን የግንዛቤ ማስጠበጫና የተሞክሮ ልውውጥ ውይይት የማጠቃለያ መድረክ አካሄደ ።
ውይይቱ ዓላማውን አድርጎ ያነገበው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር መሆኑ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተመላከተ ሲሆን የውይይቱ አጀንዳ ልዩ ትኩረት ሀገራዊና ከተማአቀፍዊ ጉዳዮች ላይ በማድረግ የሁለቱም ከተሞች የፀጥታ ሀይሎች የበለጠ በመተሳሰር ከውይይት ባለፈ በተግባር በጋራ እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታን ለማጠናከርና የሀገርን ከፍታ ለማስቀጠል መሆኑ ተገልጿል።
ክቡር ኮምሽነር ሌ/ ጀነራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ እንደገለፁት የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ህዝቡ መረጃን ለፀጥታ አካሉ በጊዜ ጥቆማ በመስጠት የሰላም ባለቤት በመሆንና ወንጀልና ወንጀሎችን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ይህን ማጠናከርና ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ጀኔራሉ አክለውም አዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ የሚለያዩ አለመሆናቸው ጠቁመው ሁለቱም ከተሞች በጋራ በመስራት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ዳር ለማድረስ እንዲሁም ቀጣይ የሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆን በማህበራዊ ሚዲያዎችና በየአካባቢው ሰላምን የሚያደናቅፉ የጸብ ፈጣሪ መረጃዎችን በመከታተልና በመቆጣጠር በጋራ በመታገል ምርጫው ሰላማዊ እና የተሳካ እንዲሆን የሁሉም ዜጎች ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የሰላም ኮንፈረንሱ እየተካሄደ ያለበት ወቅት በሀገራችን የለውጥ ችቦ የተለኮሰበት ዕለት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለው ከለውጡ ወዲህ የሚታዩ ተጨባጭ የሆኑ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ፣ የፖለቲካ ፣ የማህበራዊ ፣ የኢኮኖሚና የዘላቂ ሰላም ስብራቶቻችን እንዲጠገኑና ወደ ከፍታ እንድንጓዝ እጅግ ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑን አብራርተዋል።
ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ ሰላም ከራስ ፣ከቤተሰብ ይጀምራል ከዚያም ወደ ጎረቤትና ሀገር የሚያድግ መሆኑን ጠቁመው የሁለቱ ከተሞች ስምምነትና በጋራ መስራት ለህዝቡ የሰላም ምሰሶ ዋነኛ ጠበቆች መሆናቸውን በንግግራቸው ገልፀዋል።
የፖለቲካ ጥያቄን በጠመንጃ ለማስፈፀም ወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ምክንያት በማድረግ ብሔርና ሀይማኖትን ሽፋን አድርገው ሰላምን ለማደፍረስ የሚሞክሩ ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመከላከል የሁለቱ ከተሞች የፀጥታ አካላት ከውይይት ባለፈ በጋራ በመስራት የከተማችንን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አሳስበዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ጉዮ ገልገሎ የሸገር ከተማ ም/ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እንደገለፁት ሸገርና አዲስ አበባ ከተማ በሰላም ዙሪያ እና ወንጀሎች የሚፈጸሙበት ቦታ በጋራ በመስራት ወንጀሎችን መቀነሰ መቻላቸውን፣እንዲሁም ጠንካራ ቅንጅታዊ ስራዎች ከሸገር ከንቲባና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጋራ በመስራታቸው ለውጥ መምጣቱን አንስተው ይህን ለውጥ በማስቀጠል የሰላም ዘብ በመሆን የተጀመረውን ልማት ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ክቡር ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰለምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፣ የሸገር ከተማ ም/ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ጉዮ ገልገሎን ጨምሮ የሁለቱም ከተሞች የፀጥታ ኃላፊዎች የደንብ ማስከበሮች ፣ ሚሊሻዎች ፣ ጋቸና ሰርናዎች ፣ አባገዳዎች ፣ሀደስንቄዎች ፣ ወጣቶችኔ ቄሮዎች ተገኝተዋል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79