ለተቋም ግንባታ የአመራሩና የባለሙያዎች ትጋት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ ።
ለተቋም ግንባታ የአመራሩና የባለሙያዎች ትጋት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ ።
ሚያዝያ 10 /2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመፈጸምና የማስፈጸሙን አቅሙን በማዳበር ተልዕኮውን በተግባር እየተወጣ የሚገኝ ቢሮ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከማዕከል እስከ ታችኛው መዋቅር ከሚገኙ ፈጻሚዎች ጋር ባለፍት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ ወራት በትኩረት በሚሰሯቸው ስራዎች ላይ በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
በምክክር መድረኩ ላይ አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እንደተናገሩት ለስራዎቻችን ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሀላፊነትን የበለጠ መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበው ቢሮው በባህሪው ከሌሎች ተቋማት የሚለይበት በርካታ ባህርያትም እንዳለው አስታውሰው የሰላም የደህንነት የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ህግ ሲጣስ ህግ የማስከበር ሀገርና ከተማዋ ካለችበት የለውጥ ግስጋሴ ጋር ተያይዞ ከተማውን የሚመጥን ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ ማድረግ የተቻለው ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት አድርገን በመንቀሳቀሳችንም ነው ሲሉ አማካሪው ተደምጠዋል።
አማካሪው አያይዘውም አዲስ አበባ ላይ ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት ሆኖ የአካባቢን ሰላም ማስጠበቅ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልፀው በየአካባቢያቸው የሚያጋጥሙ ሁከቶችንና ወንጀሎችን በጋራ በመከላከልና በመሰራቱ የሚታዩ ለውጦችን መኖራቸው ማስቀጠል እንደሚገባ አብራርተዋል።
የመረጃ ልውውጡን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የሰላም ዋጋ በእጃችን መሆኑን በመረዳት በየአካባቢያችን አልፎ አልፎ የሚታዩ ክፍተቶችን በጋራ በመከላከል በቀጣይ ሀገራዊው ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ ማስረሻ ሀብቴ የቢሮው የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች የነበሩ ክፍተቶች ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ወራት ትኩረት የሚሹ ጉዳዩች ላይ ገለፃ አድርገው ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79