የፀጥታ አካል አዕምሮ ብሩህ ፣ እጁ ንፁህ ፣ ሩህሩህ ልብ ያለውና እራሱን ለለውጥ ስራ ዝግጁ ያደረገ ሊሆን ይገባል"
"የፀጥታ አካል አዕምሮ ብሩህ ፣ እጁ ንፁህ ፣ ሩህሩህ ልብ ያለውና እራሱን ለለውጥ ስራ ዝግጁ ያደረገ ሊሆን ይገባል"
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከመአከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ለዘርፉ አመራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ፣ ቡ/መሪዎችና ፈፃሚዎች በመጀመሪያ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ መስጠት ጀመረ ።
ተቋሙ የተሰጠውን ኃላፊነት በውጤታማነት ለማከናወን ይችል ዘንድ በውስጡ ያለውን የሰው ሀይል ብቁ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ሰራተኞችን ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ፣ የአሰራር ችግሮችን መቅረፍ የሚችል የሰው ሀይል ለማፍራት ስልጠናው መዘጋጀቱ በስልጠና ማስጀመሪያው ላይ ተገልጿል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ የፀጥታ አካል አዕምሮ ብሩህ ፣ እጁ ንፁህ ፣ ሩህሩህ ልብ ያለውና እራሱን ለለውጥ ስራ ዝግጁ ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለው ለአንድ ተቋሙም ወሳኝ ነገር ብቁ የሰው ሀይል ፣ የአሰራር ችግርን የሚፈታ ፣ እንዲሁም ዘመኑ በሚፈልገው ልክ እራሱን ለለውጥ ዝግጁ የሚያደርግ መሆን እንደሚገባ ገልፀው ተቋሙም ይህን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ያለውን የሰው ሀይል ብቁ ለማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም ስልጠናውን ለሚሰጠው ለኢትዮጲያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ ምስጋና አቅርበው አዲስ አበባ በፈጣን የዕድገት ጎዳና ላይ እንደመሆኗ ይህን መሰረት ያደረገ የፀጥታ ሀይል በብቁ ቁመና ላይ መኖር እንደሚገባ አስታውሰው ዛሬ ስልጠናውን የሚወስደው የቢሮው አመራርና ሰራተኛ የከተማዋን የፀጥታ ህልውና በብቃት ማስጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ረዳት ኮሚሽነር ተሻለ ሚቆሬ የኢትዮጲያ ፖሊስ ዮንቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ሰልጣኞቹ በዩንቨርስቲ ቆይታቸው በቂ ግንዛቤ እንደሚያገኙ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ሰልጣኞቹ ለተከታታይ ሰባት ቀናት የአካል ብቃትናና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና እንደሚወስዱ ተመላክቷ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79