የፀጥታ ስራዎችን ያለምንም መዘናጋት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ።
የፀጥታ ስራዎችን ያለምንም መዘናጋት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ።
ሚያዝያ 13/2018ዓ.ም (አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ )
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮና የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የከተማችን መደበኛና ወቅታዊ የጸጥታ ስራዎች ላይ ያለው የስምሪት ሁኔታዎችና አፈጻጻማቸው ዙሪያ ግምገማዊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ፣ ኮማንደር ገዛኸኝ ጌትነት የአዲስ አበበ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፣ የክ/ከተማ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ መከላከል ሀላፊዎች፣ የደንብ ማስከበር አመራሮችና የሰላምና ፀጥታ ሙያተኞችና ሌሎች የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
በግምገማ መድረኩም የወንጀል መከላከል፣ የኦፕሬሽን ስራዎች አፈፃፀም፣ የማደያዎች የነዳጅ ስርጭትና ስምሪት፣ የምርጫ የፀጥታ ስራዎች አፈፃፀም፣ ወቅቱን ማእከል ያደረገ የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስገኘታቸውን ተረጋግጧል።
በዚሁ መድረክ ላይ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የታዩ ውስንነቶች ላይ ጠንከር ያለ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ በከተማዋ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራ የፀጥታ ግብረ ሀይሉ በትኩረትና በቅንጅት እንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79