የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል የ1ኛ ሩብ ዓመት ዋና ዋና ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ
የቢሮው ጠቅላላ ካውንስል የ1ኛ ሩብ ዓመት ዋና ዋና ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ
መስከረም 27/2017 ዓ.ም
( አዲሰ አበባ )
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጠቅላላ ካውንስል የቢሮውን የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የሪፎርም ስራዎችን ገምግሟል፡፡
የጠቅላላ ካውንስሉ በውይይቱ ትኩረት ሰጥቶ የተመለከተው የ1ኛ ሩብ አመት የሪፎርም ስራዎችና እንዲሁም ዘርፎች እና ድጋፍ ሰጪ ዳይሬክቶሬቶች የቢሮ የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዘጋጅቶ ለሚመለከተው የሥራ ክፍል መላኩን፤የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ትግል ያለበትን ሁኔታ፤የተቋማት ቅንጅታዊ ስራዎች እየተመሩ ያሉበትን አግባብ እና የቴክኖሎጂ ልማት ስራዎችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቶባቸዋል፡፡
ጠቅላላ ካውንስል የዘርፍና የደጋፊ ዳይሬክተሮች በየ15ቀኑ በጋራ የሚሰበሰቡበት የውይይት መድረክ ሲሆን ውይይቱን የመሩት አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት በሩብ ዓመቱ ቢሮው የለውጥ መሳሪያዎችን ተጠቅሞ ለመሥራት ባደረገው ጥረት በአመራሩና ሰራተኛው መካከል ያለው መስተጋብር እየተሻሻለ መምጣቱን፤ የአብዛኛዎቹ ግቦች አፈፃፀም ከ100% በላይ መሆኑንና የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር መከላከል ተግባራት ላይ የአፈፃፀም መሻሻል እየታየ መምጣቱን ገልፀዋል::