7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መላው የጸጥታ አካላትና አጋዥ ሀይሎች ከወትሮው በበለጠ መልኩ አቅምን አጠናክሮ ማስኬድ ይገባል ።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መላው የጸጥታ አካላትና አጋዥ ሀይሎች ከወትሮው በበለጠ መልኩ አቅምን አጠናክሮ ማስኬድ ይገባል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ

ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ፣ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከጥበቃ ሰራተኞች ፣ከሞተር ማህበር አባላት በቅንጅትና በመናበብ ረገድ ከወትሮው በላቀ መልኩ በወንጀል መከላከልና መቆጣጠርና ሰላማዊ ምርጫና አጋዝ የጸጥታ አደረጃጀቶች ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በ11ዱም ክ/ከተሞች በሁለት ዙር የሚጠናቀቅ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት በከተማው ላይ የተከናወኑ ሀገር አቀፍና ከተማ አቀፍ ሁነቶች ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት ብሎም ሰላም ወዳጁ ማህበረሰብ በሰላም ወቶ እንዲገባ ስራዎች ሲስሩ እንደነበር አስታውሰው በከተማው ዘላቂ ሰላም የሰፈነበት የከተማው ነዋሪ ስለ ሰላም ያለው ትኩረት የጨመረበት የሰላም መርህ ተመሳሳይ ዕሳቤ የያዘበት የወንጀል መከላከል ስራው ከነዋሪው ጋር በጋራ በመሆን እርብርብ የተደረገበት በየጊዜው ከተማው ለማጥቃት የተለያዩ አካላት ትኩረት ቢያደርጉም በመላው ነዋሪና የጸጥታ አካላት ብሎም ከጸጥታው አጋዝ ሀይሎች ጋር በመሆን የታሰቡና የታቀዱ የጠላት ሀይሎችን ሴራ መመከት መቻሉን በዝርዝር ተናግረዋል።

ኃላፊዋ አክለውም የተቋማት ደህንነት አጠባበቅ ፋይዳው የጎላ እንዲሆን የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ከጸጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀትና በማስቀጠል የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት በማጠናከር ሰላም ወዳዱ ነዋሪ በገንዘቡና በዕውቀቱ የቅጥር ጥበቃን ወደ ስራ በማስገባት አካባቢውን እየጠበቀና የህግ የበላይነት ማረጋገጥ መቻሉን ገልጸው ።

መጭው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ምድር ስር የህዝብ ሉአላዊነት የሚረጋገጥበት ሀገረ መንግስት የሚጸናበት ዲሞክራሲ የሚሰፍንበት እንዲሆን የጸረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍና አካባቢን በንቃት በመጠበቅ ከመደበኛ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመናበብና ስምሪት በመውሰድ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ኃላፊዋ አሳስበዋል።

አቶ ክፍሌ ለማ የቦሌ ክ/ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው የከተማው ልማት ባለፉት አመታት ከነበረበት ውጣ ውረድ በተለየ መልኩ በመላቀቅ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በተገባው ቃል መሰረት እየተሰራ ይገኛል ብለው ወቅቱ ቀጣይ ኢትዩጵያዊያን በጉጉት የሚጠብቁት ምርጫን በድል በማጠናቀቅ ፈር ቀዳጁ የዲሞክራሲ አንድምታ በማምጣት በሀሳብ በመምከር የሚያምን የብልጽግና ጉዞ እንዲረጋገጥ የከተማን ክብር በመስጠት በትብብር በመስራት የከተማው ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

ዶ/ር ወንድማገኝ ታፈሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ ውይይቱን ሲመሩ እንዳሉት ስልጠናው በዋናነት ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲያልፍ የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲዎችና ማህበራት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ስልጠናውን በሁለት ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት በጋራ በመሆን ያዘጋጁት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል ።

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!

ለፀጥታ መረጃ:--

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7