ወንጀል ድንበር የለሽ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ የሰላም ሰራዊትና የጋቸና ሲርና ህዝባዊ አደረጃጀቶች ቅንጅታቸውን በማጠናከር የፀጥታና የደህንነት ስራን በጋራ እንዲሰሩ አቅጣጫ ተሰጠ።
ወንጀል ድንበር የለሽ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማና የሸገር ከተማ የሰላም ሰራዊትና የጋቸና ሲርና ህዝባዊ አደረጃጀቶች ቅንጅታቸውን በማጠናከር የፀጥታና የደህንነት ስራን በጋራ እንዲሰሩ አቅጣጫ ተሰጠ።
ወንጀል በመከላከልና የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ ስራ የተሰማሩ የሰላም ሰራዊትና ጋቸና ሲርና የህዝብ አደረጃጀቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ እንዲሁም በቂርቆስ ክ/ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአንድ መአከል የስራ ስምሪት ተሰጠ ።
ክብርትወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ተግባራችንን በትኩረት ስምሪታችንን በንቃት ማድረግ ስንችል ከተማችን ከወንጀል ነፃ ማድረግ እንችላለን ያሉት ሲሆን ጨለማን ተገን ተደርጎ የሚከናወኑ ወንጀሎችን ለመቀነስ የተጀመሩ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል።
ኃላፊዋ አክለውም በከተማችን ዘላቂ ሰላም ማምጣት የተቻለው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ መሆኑን አውስተው የሚታየውን ሰላም ማረጋገጥና ማፅናት የሚቻለው ቅፅበታዊ የሆነውን የፀጥታ ሁኔታ በትኩረት በመመልከትና መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።
ትላልቅ ሀገራዊ ሁነቶች በድል እንደተጠናቀቁ ሁሉ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ህዝባዊ አደረጃጀቱ ከመደበኛው የፀጥታ መዋቅር ጋር በቅርበት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (PSAB)
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!
ለፀጥታ መረጃ:--
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79