የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ከ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ እስከ ወረዳ ላሉ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ሰጠ።
የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ከ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ እስከ ወረዳ ላሉ የዘርፉ አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ሰጠ።
..........
ግንቦት 24 የሚካሄደው 7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የሚያግዝ የቅድመ አዝማሚያና ስጋት ልየታ በማድረግ ወደስራ መገባቱን የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ ገልፀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ዘመኑ የሚጠይቀውን ፈጣን ቀልጣፋና ታማኝ መረጃን በማድረስ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለሙያ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በዘርፉ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ሲሰሩ የነበሩ የፀጥታ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና የቅንጅት ስራውን በማጠናከር ሁሉም ባለሙያ በጥብቅ ዲሲፕሊን የተመራ የፀጥታ ስራውን እንዲሰራ ዶ/ር ወንድማገኝ አሳስበዋል።
ህብረተሰቡ ለሚገጥመው እያንዳንድ መረጃና ጥቆማ በ8882 ነፃ የስልክ መስመር 24 ሰአት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ተመላክቷል።
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም (PSAB)
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!
ለፀጥታ መረጃ:--
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79