የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

መስከረም 30/ 2017 ዓ.ም

(አዲስ አበባ)

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመግሟል ::

በግምገማዊ ውይይቱ ላይ ከወረዳ እስከ ማዕከል ያሉት የዘርፉ ሰራተኞች ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን ውይይቱን የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይዎት በለጠ መርተውታል፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የግብ ስኬት፣ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ያጋጠሙት ችግሮች፣ የተሰጡ መፍትሔዎች....ወዘተ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አቶ ውድነህ አቢ የዘርፉ ዳይረክቶሬት ባለሙያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መድረኩን የመሩት የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር ወ/ሮ ፍረህይዎት በለጠ በዚህን ወቅት እንደተናገሩት ህብረ ብሄራዊነታችን የሚያጠበቁ አንድነታችንን የሚያጠነክሩ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው ማለፋቸው ቅንጅታችንን አጠናክረን በመስራታችን ነውና አሁንም ይህ የአፈፃፀም ብቃታችን በዚሁ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።