ቢሮው ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች "በሰላም ዕ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች "በሰላም ዕሴት ግንባታ የወጣቶች ሚና"በሚል መሪቃል ስልጠና ሰጠ።

ቢሮው ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች "በሰላም ዕሴት ግንባታ የወጣቶች ሚና"በሚል መሪቃል ስልጠና ሰጠ።

ጥቅምት 01/ 2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

*** ***

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴትና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ "በሰላም ዕሴት ግንባታ የወጣቶች ሚና"በሚል መሪቃል ከ11ዱ ክ/ከተማ የተወጣጡ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ስልጠና ሰጥቶዋል ።

መድረኩ ላይ በመገኘት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ ባለሙያ አቶ ኤልያስ ቀጄላ ፦ የሰላም ምንነት፣ የሰላም ግንባታ አተያየቶች፣ ሰላምና ወጣትነት፣ በሰላም ግንባታ የወጣቶች ሚና በሚሉ ርዕሶች ላይ ስፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል ::

የሰላም ዕሴት ግንባታ የረጅም ጊዜ ሂደትን የሚጠይቅና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን የሚያካትት መሆኑን ጠቅሰዉ ወጣቶች ሁሉን አቀፍ አቅማቸዉን ለሰላም ግንባታ በማዋል ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል::

መድረኩን የመሩት የዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ተመስገን እጅጉ ሲሆኑ የተለያዩ የአደባባይ በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብረው ማለፋ ቸው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ሚና ስላለበት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ::

በተለይም ወጣቶች ደግሞ የህብረተሰቡ የማይነጥፍ ክንድ በመሆናቸው ግጭት ከመከሰቱ በፊት በባሕላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች በመጠቀምና በመወያየት ለሰላሙ ዘብ መቆም ይኖርበታል ብለዋል።