"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ህዝብን ባለቤት በማድ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ህዝብን ባለቤት በማድረግ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች በቅንጅት ማከናወን ሲቻል ነው"

"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ህዝብን ባለቤት በማድረግ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች በቅንጅት ማከናወን ሲቻል ነው"

          ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ      አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 

ሰኔ 25/2018 ዓ.ም 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ  የፀጥታና የደህንነት   ጉዳዮች ፣ በድህረ-ምርጫ  ሥራዎች እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ላይ ከድህረ-ምርጫ ጋር ተያይዞ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የተከናወኑ የሰላምና የደህንነት ሥራዎች ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይ ወቅት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይም የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ  እንዳሉት የከተማን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ህዝብን ባለቤት አድርጎ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን በቅንጅት ማከናወን ሲቻል መሆኑን ገልፀው በቅድመ  ምርጫና በምርጫ ወቅት የነበሩ የፀጥታ ስራዎችን አቀናጅቶ ከመሄድ አኳያ በድህረ ምርጫ ላይ መቀዛቀዞች እንዳይኖርና የወንጀል ድርጊቶች እንዳይበራከቱ   የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል።

በተለይም ከሃይማኖትና ከሰላም ዕሴት ግንባታ አንጻር በሃይማኖት ተቋማት "በመከባበርና በአብሮነት ለሰላም ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማጠናከር፣ በቴክኖሎጂ የተደራጁ  የሃይማኖት ተቋማት መረጃዎችን ማደራጀትና በዘርፉ የታዩ ለውጦችን መገምገሙንም የቢሮው ም/ል ቢሮ ኃላፊና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር አቅርበዋል።

ሀላፊው አክለውም በሃይማኖት ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር በመገምገም የተግባር አቅጣጫዎች የተሰጡ ሲሆን፣ በለማ ቴክኖሎጂዎችን  ግልፀኝነት  በመፍጠር  ወደ ስራ የተገባበትን አግባብ  ላይ  በዝርዝር አቅርበዋል።

በክ/ከተሞችና በወረዳዎች ላይ  ከፀጥታ ስራና ከወንጀል መከላከል  ጋር በተያያዘ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች  ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በቀጣይ ወራቶች በርካታ ሀገራዊና ከተማ አቀፋዊ ኩነቶች እንደመኖራቸው የፀጥታ ስራዎች እጅግ በተናበበና በቅንጅት  በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ ያሳስቡት የቢሮ ኃላፊዋ  በቀጣይ  አቅጣጫ :-

-በመጨረሻም በክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን ሲያስቀምጡ  ብሎክን መሰረት ያደረገ  የሰላም ሰራዊት  የአንድ ማዕከል ስምሪት መስጠትና በቴክኖሎጂ  የታገዘ የሰላም ስራዊት መረጃን ማደራጀት ፣  ሀይማኖትን ሽፋን ያደረጉ የፅንፈኝነትና የአክራሪነት መንፈስን መታገልና ማስቆም ፣  የሚዲያ ተቋማት ላይ የሚሰራጩ  ሀሰተኛ መረጃዎችን  መታገል ፣ የወንጀል መከላከል ስራን ማጠናከር  ፣   የፀረ ሰላም ሀይሎችን መቆጣጠርና መከላከል የመረጃ  ቅብብሎሽን ማዘመንና ማቀላጠፍ ፣  የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን አበክሮ መስራት ፣  የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ ሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪዎች  በመቆጣጠር በአጥፊዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ  መውሰድ ፣  የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግና የሪፎርም ስራዎችን በውጤታማነት መፈፀም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ አስቀምጠዋል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157