በተያዘው በጀት አመት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያን የፈጣን ምላሽ ስርአትን በመዘርጋት በተሰሩ የፀጥታና ኦፕሬሽን ስራዎች የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል።
በተያዘው በጀት አመት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያን የፈጣን ምላሽ ስርአትን በመዘርጋት በተሰሩ የፀጥታና ኦፕሬሽን ስራዎች የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ
ሰኔ 26/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ በተያያዘ በጀት አመት እንደ ዘርፍ አቅዶ ያከናወናቸውን ተግባራት ከማዕከል እስከ እታችኛው መዋቅር ድረስ ካሉ ባለሙያዎች ጋር ምክክርና ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ መድረክ ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት በተያያዘ በጀት አመት እንደ ቢሮም እንደ ዘርፉም በመቀናጀት በከተማው ላይ የተከናወኑ በረካታ ሀይማኖታዊ ብሔራዊና አለም አቀፍዊ አህጉራዊ ሁነቶችን ጨምሮ በቅርቡ የተካኔደውን አቀር አቀፍ ምርጫን ሳይቀር ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር ማከናወን መቻሉን ገልፀዋል።
ወንጀልና ወንጀል ነክ የሆኑ ዝርፊያዎች ህገ ወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውሮች ከባባድ ወንጀሎችን ጨምሮ ከአጋዥ ሀይሎች ጋር በመናበብ በተጠናከረ ስራ በመሰራቱ አመርቂ ውጤት እንደተመዘገበ የገለፁት የዘርፉ ሀላፊው የግልና የመንግስትን ተቋማት ከሚጠብቁ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች ላይም የተሰራው ስራ አድንቀው የወንጀል መፈልፈያ የነበሩና ለከተማው የጸጥታ ስጋት ሲፈጥሩ የነበሩ ህገ ወጥ ድርጊት ሲያከናውኑ የነበሩ ግለሰቦች ወደ መደበኛ ስራ እንዲገቡ ማሰማራት መቻሉን፣ ከሸገር ሲቲ ጋር የወንጀል መከላከልና የፅንፈኞችን ሴራ ማክሸፍ መቻሉን ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የአካባቢን ሰላም ማስጠበቅና ወንጀለኞችን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ፣ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች የጸጥታ አካላት የጸጥታ ባለሙያዎች በተጨማሪ ከአጋዥ የፀጥታ ሀይሎች ጋር በተቀናጀ መልኩ በመቀናጀት የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ተችሏል ሲሉ አቶ ተስፋዬ ደንድር አብራርተዋል።
ሀላፊው አያይዘውም በበጀት አመቱ የጸጥታው ስራ እጅግ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት እንደ መሆኑ
መጠን ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል የጸጥታ ስራ ሁሌም ክትትል የሚሻ መሆኑንም ጠቅሰው ሀገራዊ ምክክር ኮምሽንን ጨምሮ የመንግስት ምስረታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ትኩረት ሰቶ በመንቀሳቀስ ህብረተሰቡን የማሳወቅ ስራው አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሀገርን ዕድገትና ሀያልነት የማይፈልጉ በርካታ የጠላት ሀይሎች ሴራን በከተማው ላይ በተለያየ ጊዜ ስለሚንቀሳቀሱ እንደ ወትሮው ሁሉ ሴራቸውን በማክሸፍ በንቃት በመጠበቅ በድክመታችን በመግባት እኩይ ሴራቸውን እንዳይፈጽሙ በውይይት በንግግር በመግባባት ለከተማው ሰላም ብልጽግና መረጋገጥ በጋራ በመቀናጀት መስራት እንደሚጠበቅ የውይይቱ ተሳታፊዎች የገለፁ ሲሆን ለዓላማው መሳካትም በንቃትና በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ኢንስፔክተር ፍቃዱ አቶምሳ የዘርፉ ዳይሬክተር በበኩላቸው ስራችን ላይ ትኩረት በማድረግ ሀላፊነትን በይበልጥ በመወጣት ከመላው የጸጥታ መዋቅርና ከጥምር የጸጥታ ግብረ ሀይሉ ጋር በመቀናጀት ግንባር ቀደም በመሆን የከተማውን ነዋሪ ከሚያማርር ለጸጥታው መደፍረስ ስጋት ከሚሆኑና ከሆኑ ድርጊቶች በቻልነው አቅም ሁሉ ህብረተሰቡን መከላከያ ይገባናል ሲሉ ተደምጠዋል።
ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት ጥንካሬዎች ድክመቶችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ያደረጉት አቶ ዳምጠው አያሌው የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ከመድረኩ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰቷል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157