የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ። 

               04/11/2018 ዓ.ም (PSAB)
                 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የጸጥታ ተቋማት ከመደበኛ የሰላምና ደህንነት ስራዎቻቸው ጎን ለጎን፣ ለትውልድ ተሻጋሪ በሆኑ የልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ኃላፊዋ በንግግራቸው ወቅት እንደ ሀገር ባለፉት ዓመታት 48 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፤ በዚህ ታላቅ አገራዊ ንቅናቄ 90 ሚሊዮን የሚሆኑ በአረንጓዴ አሻራ የተራቆቱ አካባቢዎች ዳግም አረንጓዴ መልበስ መቻላቸውን ገልጸዋል። ይህ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ልማትም ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ይበልጥ ምቹና ማራኪ እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል።

ለትውልድ እዳን ሳይሆን የብልጽግና ምንዳን ማውረስ ይገባል ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፤ የጸጥታ ተቋማት አባላት በዚህ ታሪካዊና የጋራ አሻራ በሚያኖር የልማት ሥራ ላይ በከፍተኛ ደስታ፣ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉም ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ አለመሆኑን አስገንዝበው፤ የተተከሉት ችግኞች በሙሉ ጸድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲበቁ በየደረጃው የሚገኘው አካል በተከታታይ የመንከባከብ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል።

የከተማው ውበት አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ በመርኃ ግብሩ በመገኘት የከተማችንን አረንጓዴነት፣ የነዋሪዎቿን ተስፋን የምንተክልበት በመሆኑ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅብንና የተተከሉ ችግኞች የነገዋን አረንጓዴ ኢትዮጵያ የሚገነቡ አሻራዎች ሲሆን፣ በተቀናጀ የህዝብ ተሳትፎ የሚከናወኑ ተግባራት ለሀገር እድገትና ለትውልድ ተጠቃሚነት ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሚተከሉ ችግኞችን በጥንቃቄ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መትክል እንደሚገባ አደራ ጭምር አሳስበዋል።

መርሃ ግብሩ የአረንጓዴ ልማትን በማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ ንጹህና ምቹ አካባቢ ለማስረከብ የብልፅግና ፓርቲ የልማትና ዘላቂነት እሳቤን በተግባር የሚያሳይ መሆኑ የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ ተገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ  የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የቢሮው ከመአከል እስከ ወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157