የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝቡና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ በአዲስ አበባ ከተማ የታቀዱ የጥፋት ሴራዎችን በማክሸፍ ፍጹም ሰላማዊ ከተማ ማድረግ ተችሏል።
የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝቡና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ በአዲስ አበባ ከተማ የታቀዱ የጥፋት ሴራዎችን በማክሸፍ ፍጹም ሰላማዊ ከተማ ማድረግ ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
7/11/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠሪ ተቋሙ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የ2018 በጀት የእቅድ አፈጻጸም ከማእከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ጋር የግምገማ መድረክ አካሄዱ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንደገለፁት በበጀት አመቱ የሰላም፣ጸጥታና ደህንነት ስራዎች በመሰራቱ በከተማዋ ትላልቅ ሐይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ኩነቶች በሠላም መጠናቀቃቸውን በመግለጽ ከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶች ያለ ምንም የጸጥታ ችግር እንዲያልፉ በቅንጅት ተሰርቶ ከተማዋን ለቱሪስት መዳረሻ የስበት ማእከል ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።
የተቋም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር የአመለካከትና የክህሎት ስልጠና በመስጠት ሁለንተናዊና መዋቅራዊ ሥራዎች በትኩረት የተሰሩበት ዓመት መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ገልፀው ፣ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ የሚረዳና የአገልግሎት አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚያቀላጥፍ ሰራተኛ በመፍጠር ረገድ በዓመቱ ስኬታማ ሥራ ተሰርቷል ሲሉም ገልፀዋል።
ቢሮ ሀላፊዋ አክለዉም የጸጥታ መዋቅሩ ከህዝቡና ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ አዲስ አበባ ከተማ ፍጹም ሰላማዊ እንድትሆንና የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማስቻል ተችሏል ብለዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ የፀጥታ ስራዎች በስኬት የታጀቡና በከተማዋ የተካሄዱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች፣ የአደባባይ በዓላትና ሌሎች ዝግጅቶች በሰላም መጠናቀቃቸው ተናግረዋል። በተቋም ግንባታ ስራ ብቁ የሆነ አመራርና ሰራተኛ ማፍራት መቻሉን አንስተው ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን መሰራቱን ገልፀው አክለውም በደንብ ማስከበርና የደንብ ጥሰቶን ከመመከት አኳያ መሬት የያዘ ተጨባጭ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በሁለቱም ተቋማት በበጀት አመቱ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በመከወን የደንብ ጥሰትን የሚጸየፍ ህብረተሰብ መፍጠር መቻሉና የተቋም ግንባታ ስራ ላይ በልዩ ትኩረት በመሰራቱ አገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል መቻሉ ፤ የህግ የበላይነትና ወንጀል መከላከል ስራዎችን ፈር በማስያዝ የህገ-ወጥ መሬት ወረራ፣ ህገ-ወጥ ግንባታ የደንብ ጥሰቶችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉ በቀረበው ሪፕርት ተመላክቷል።
የመረጃን እውነታ ከስሩ በማጥራት ብልሹ አሰራርን መከላከልና ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከል ከተለያዩ የፀጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲሁም ዘመናዊና ወቅቱን የዋጀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስኬታማ ሥራ የተሰራበት ዓመት እንደነበርም የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157