በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! የመጣው ድል በቅንጅት በተሰራ ስራና ውጤት በመሆኑ እሱ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! የመጣው ድል በቅንጅት በተሰራ ስራና  ውጤት በመሆኑ እሱ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል። 

 ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ 
             
               
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ በተካሄደው ምዘና ውስጥ ካሉ ቢሮዎች ከፍተኛ ውጤት በማምጣትና አንደኛ በመውጣት በከተማው አስተዳደር የመኪና ሽልማት ተበርክቶለታል ። 

ይህንን በማስመልከት የቢሮው ሀላፊዋ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  ለቢሮው አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች ባስተላለፉት መልዕክት ለተከታታይ አራት  አመታት ውጤት በማምጣት በኩል ቢሮው ከተማው ላይ ካሉ ተቋማት ግንባር ቀደም መሆኑን አስታውሰው በስራችን ላይ ሁሉ ከፊት በመቅደምና የምንሰራው ስራ በማገዝ አሁን ላይ ለደረስንበት ውጤት ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና ይገባው ብለዋል።

ተልዕኮን በመቀበል  በአመራሩና በፈጻሚዎች አማካኝነት ተቋሙ በርካታ ስራዎችንና ችግሮችን በማለፍና በማከናወን የመፈጸምና የማስፈፀም አቅሙን በማጠናከር በከተማውን  የጸጥታና የደህንነት  ስራ በልዩ ሁኔታና በቁርጠኝነት የተሰራበት አግባብ ውጤታማነት፣  ቢሮው ሪፎርም በማድረጉ ዕቅድን አልቆ በመፈፀም ውጤታማ መሆኑና  ለስኬቱ መነሻ መሆኑን ገልጸዋል ።

ሀላፊዋ አያይዘውም ሕዝቡን ያሳተፈ የጸጥታና የመረጃ ስርአት የተጠናከረበ፣  አደረጃጀት ጉልቶ የወጣበት፣  የኦፕሬሽን ስራ በደንብ የተመራበት ፣ የጠላትነት ሴራ ማክሸፍ የተቻለበትና  7ኛው  ሀገራዊ ምርጫን ጨምሮ በከተማው ላይ የተከናወኑ በርካታ ሁነቶች በስኬት የተጠናቀቁበት ባጠቃላይ የተቋሙን ራዕይ በማሳካት ፍሬ ማፍራት በመቻሉ የተገኝው  ውጤት ነው ብለዋል።

ይህንን የተገኝ ውጤት በቀጣይም አጠናክሮ በማስቀጠል ለትውልድ የሚተላለፍ ስራ በጋራ በመስራታችን ኩራት ሊሰማችሁ ሊሰማን ይገባልም በማለት በቅንጅት የመጣውን ድል የበለጠ በማስቀጠል ተቋሙን በመገንባት የተቋሙን ግንባታ ማስቀጠልና የከተማውን ሰላምና ጸጥታ አጽንቶ ማስኬድ ይገባልም ሲሉ ሀላፊዋ በአደራ ጭምር ገልጸዋል።

ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157