ለሰላም ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለሰላም ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ለሰላም ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ጥቅምት 06/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ በአገር በቀል የግጭት አያያዝና አፈታት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከ11ዱ ክ/ከተማ ለተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና ሰጥቷል።

ለግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀውን ሰነዱ ያቀረቡት የዘርፉ የስልጠና ባለሙያ ወ/ሮ አዲስ ዓለም ዘነበ የሰላምና የግጭት ምንነት፣ የግጭት መንሴዎች፣የባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ማለትም ሽምግልና ወይም ዕርቅ፤ድርድር፤ምክክር ትብብር.ወዘተ ርዕሶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ አዲስ ዓለም በማብራሪያቸውም ፍትሃዊነት በሌለበት አዎንታዊ ሰላም አለ ማለት እንደማይቻል ጠቁመው በየትኛውም መስክ ፍትሃዊ አሰራርን ማስፈን ይገባል ካሉ በኃላ ግጭት ተፈጥሮአዊ ስለሆነ መፋታትና ማስተዳደር እንጂ ጨርሶ ማስወገድ አይቻልም በማለት ገልፀዋል።

መድረኩን የመሩት የዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ ተመስገን እጅጉ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የህብረተሰቡን ግጭትን አስቀድሞ የመከላከልና የማስተዳደር ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሰላማዊ አኗኗርን ማስፈን ስለሚገባ ይህ ሥልጠና ተዘጋጅቷል ብለዋል።

አቶ ተመስገን አክለውም በባህላዊ ዘዴዎች ግጭትን መፍተት በአገራችን ቀድሞ የነበረ እና አሁንም ያለ ዕሴታችን በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።