የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት እንደ ዘርፍ አቅዶ ያከናወናቸውን ተግባራት ከማዕከል እስከ እታችኛው መዋቅር ድረስ ካሉ ባለሙያዎች ጋር ምክክርና ውይይት አድርጓል።
ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረግና የከተማውን ሰላም የማረጋገጥ ስራ በቀጣይም አጠናክሮ ማጠናከር ይገባል ።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት እንደ ዘርፍ አቅዶ ያከናወናቸውን ተግባራት ከማዕከል እስከ እታችኛው መዋቅር ድረስ ካሉ ባለሙያዎች ጋር ምክክርና ውይይት አድርጓል።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት በዋነኝነት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና ከአጋዥ የጸጥታ ሀይሎች ፣ የከተማው የሰላም ዘብና አምባሳደር ከሆኑት የሰላም ሰራዊቶች አጠቃላይ ከመላው ነዋሪ ጋር በመቀናጀትና ተናባቢ በሆነ መንገድ ስራዎች ላይ በማተኮር ስኬታማ ስራዎችን መስራት እንደተቻለ ገልጸዋል።
ህዝባዊ በዓላት በደንብ በተመራና በተቀናጀ መልኩ በመስራት የመረጃ ቅብብሎሽ በተደረገ የኦፕሬሽን ስራ በነበረ ትጋት የጸጥታ ስራዎች በውጤታማነት የተከናወኑበት ወንጀሎች ይፈጸሙ የነበሩበትን ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም ወንጀል ነክ የሆኑ ድርጊቶች የቀነሱበትና ህብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች በማድረግ ነዋሪው እርስ በርስ በመግባባት ሰላም እንዲሰፍን ለሰላም ለልማት ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲተጉ ማድረግም እንደተቻለ አቶ ፍስሐ አብራርተዋል።
ሀላፊው አያይዘውም በቀጣይ አመትም ባሳለፍነው በጀት አመት የተገኝውን ስኬት አጠናክሮ በማስቀጠል የጸጥታ አጠባበቅ ስራዎችን በማጠናከር ነዋሪውን ያሳተፈ ስራዎችን በማጠናከር ለከተማው ሰላም መረጋገጥ በትኩረት መስራት ይገባል በማለት የቀጣይ የስራ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።
አቶ አብርሃም እንግዳወርቅ የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዘርፍ በ2018 በጀት አመት ምን አቅዶ ምን አሳካ በማለት የተከናወኑ ተግባራትን የነበሩ ጥሩ ጎኖችና ክፍተቶችን በዝርዝር አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157