በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የሰላም እሴት ግንባታ ሥራ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የሰላም እሴት ግንባታ ሥራዎች በከተማዋ ሰላም እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አዎንታዊ አበርክቶ እንደነበራቸው ተገለፀ ።

በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የሰላም እሴት ግንባታ ሥራዎች በከተማዋ ሰላም እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አዎንታዊ አበርክቶ እንደነበራቸው ተገለፀ ።
  *
   ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ እና የ90 ቀን እቅድ አቅጣጫ ማስቀመጫ መድረክ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የዘርፉ አስተባባሪዎች ጋር አካሂዷል።
         
አቶ ብርሃኑ ረታ   የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ  መድረኩን ሲያስጀምሩ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የሰላም እሴት ግንባታ ሥራዎች በከተማዋ ሰላም እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አዎንታዊ አበርክቶ እንደነበራቸው ገልጸው  የውስጥ አመራሩምና ፈፃሚው በመናበብ፣  በመደማመጥ እና ለውጤት በመትጋት የተዋሃደ   መሆኑ ፣  ጠንካራና ችግር ፈቺ የድጋፍና ክትትል ስርዓት ያለው (7/24) የሚሰራ ተቋም መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።  

ሀላፊዉ  አያይዘውም በየደረጃው በሚገኘው ማኅበረሰብ ውስጥ አዎንታዊና ሀገር በቀል እሴቶች እንዲጎለብቱ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ በማንሳት ከተማዋ ውስጥ አንዱ ከአንዱ እየተማረ የሚሄድበትን፣ የሚዳሰስና የሚጨበጥ ውጤት ያመጣ የሰላም እሴት ግንባታ መድረኮችን በመፍጠር ህብረተሰቡን የሰላሙ ባለቤት ማድረግ ስለመቻሉ ጠቁመዉ  የሥራችን ዋና ውጤት የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣትና ሕዝቡን የሰላሙ ዋና ባለቤት ማድረግ ነውም ብለዋል።

አቶ ብርሃኑ  አክለውም በበጀት ዓመቱ ከመንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነት ወሰን አንጻር ህግን መሠረት ያደረጉ አሰራሮችን በመከተል፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በቅርበትና በትስስር በመሥራታችን ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቁ በማድረግ  ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች እንዳይስፋፉ፣ በሀገር ጉዳይና በትውልድ ግንባታ ላይ አዎንታዊ እሴት እንዲመጣ ጠንካራ ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን  ገልፀው በቀጣይም ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

 ከዚህ ቀደም አድካሚ የነበረውን የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት በማሻሻል፣ በፈጠራና በፍጥነት የታገዘ አሰራር መዘርጋቱን ጠቁመው፤ በቀጣይም እንደ ‘ዓውደ-ሰላም’ እና ዲጂታል ፒስ ቢዉልዲንግ  ያሉ ዘመናዊ የሰላም ግንባታ ስልቶችን በመጠቀም ሰላምን የሁሉም አጀንዳ በማድረግ ፍጹም ሰላምን ለማረጋገጥ እና ለ2019 በጀት ዓመት ይበልጥ በመዘጋጀት ውጤቱን ለማጠናከር እንደሚሰራ አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣ በተቀረበው ሪፖርት ላይ ከታችኛው መዋቅር ከመጡ አስተባባሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችን ለማረም የሚያስችል አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን፣  የ90 ቀን የትኩረት እቅድ አፈጻጸም ላይም የጋራ መግባባት  ላይ በመድረስ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157