የቀጠለ

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቀጠለ

የአዲስ አበባ ከተማ የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር  ክላስተር የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን  ሲገመግም አዲስ አበባን የሰላምና የህብረ-ብሔራዊ አንድነት ተምሳሌት ከተማ እንዲሁም ለቱሪዝምና ለዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተመራጭ መዳረሻ የስበት ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና በዚህም አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጿል።

የክላስተሩ ሰብሳቢና የከተማ አስተዳደሩ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክላስተሩን አፈፃፀም በገመገሙበት ወቅት  የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።
 
እነሱም
*  ከሰላምና ፀጥታ ስራ አንፃር :-

የህብረተሰቡ የሰላም ባለቤትነትን በማስቀጠል   የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን ማጠናከር  ፣ የከተማችንን የሰላም ከተማነቷን ማስቀጠልና የተቋም ግንባታ ስራዎቻችንን ማጠናከርና  አስቻይ ሁኔታዎችን  መፍጠር  ፤ የልማት የመልካም አስተዳደር የህግ የበላይነትን አጠናክሮ በማስቀጠል ነዋሪው ፍላጎት ማርካት

* ከደንብ ማስከበር ስራዎች አንፃር:-

የደንብ ጥሰት የሚጠየፍ ማህበረሰብና ኦፊሰሮች መፍጠር  የኮሪደር ልማት ስራ ጥበቃን ማስቀጠል  እንዲሁም  ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የደንብ ጥሰቶችን መከላከል ፤ የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ማስፍት
 
*   ከንግድ ስርአትና ቁጥጥር ስራዎች አንፃር፡-
 
የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጥሩ ነጋዴዎች አስተዳደራዊ መፍትሔ መስጠት፣  የተጀመሩ ስራዎችን የርብርብ ማዕከል ማድረግ ፤ የምሽት ንግድ ቁጥጥር ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ፣ነጋዴዎች ህጋዊ የንግድ ስርአትን እንዲከተሉ የድጋፍና ክትትል ስራ መስራትና ህግን ተላልፈው በሚገኙት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነተ ማረጋገጥ
 
* ከስነምግባርና ከፀረሙስና ስራዎቻችን አንፃር ፡- ሙስናን የሚጠየፍ ማህበረሰብ መፍጠርና አመራሩም ከሙስና የፀዳ አሰራርን ተግባራዊ የሚያደርግና ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ጥብቅ የሆነ ክትትል ማድረግ
 
* ከፍትህ አንፃር፡- የህግ የበላይነት በማረጋገጥ የዜጎችን በሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
 
*  ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አንፃር፡- ከተማችን ላይ የሚፈጠሩ እሳት አደጋዎችን የመቆጣጠር አቅም ያለው ተቋም መፍጠርና የቅድመ መከላከል ስራዎች በትኩረት መስራት
 
*  ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጣችን አንፃር፡- በከተማዋ የትራንስፖርት ፍሰቱን መቆጣጠርና በተርሚናል አካባቢዎች ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህረተሰቡን ከእንግልት መታደግና ከታሪፍ በላይ የሚጠይቁ ትራንስፖርት ሰጭዎች ላይ አስተዳዳራዊ እርምጃ መውሰድ
 
*  ከፅዳት ስራዎቻችን አንፃር፡- ከተማችን አዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገችና ለመ፣ኖሪያና ለመዝናኛ ተመራጭ ከተማ እየሆነች እንደመምጣቷ ከተማዋን የሚመጥን የፅዳትና የውበት ስራዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ተግባራዊ ማድረግ  

*  ከሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎቻችን አንፃር ፡- የመንግስትና የህዝብን ጥቅም የሚያሳጡና እርስ በርስ የሚያጋጩ  ሀሰተኛ መረጃን በመታገል ትክክለኛና ታማኝ መረጃን ማድረስ ፤ ለህብረተሰቡ ስጋት የሚፈጥሩ መረጃዎች የሚያሰራጩ አካላትን በመቆጣጠር እውነተኛውን መረጃ መስጠት ይገባል።
 
*  ተቋማት ከከተማዋ ፍላጎት አንጻር የደረሰችበትን ሂደት የሚመጥን የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ፤ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር፣ድጋፍና ክትትልና ጋር ትኩረት አድርጎ ማስቀጠል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አድርገው አስቀምጠዋል።

ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157