የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከልደታ ክ/ከተማ እስልምና ምክር ቤት ጋር በመሆን በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአራት የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት አስጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ  ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከልደታ ክ/ከተማ እስልምና ምክር ቤት ጋር በመሆን በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የአራት የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት አስጀመረ።

ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅና በማስጠበቅ እንዲሁም የቅድመ ወንጀል  ስራዎችን ከመስራት በተጨማሪ   ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን  አካቶ በመያዝና  በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር  ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ። ዛሬም በልደታ ክ/ከተማ  የአራት አቅመ ደካሞችን  ቤት ሙሉ በሙሉ በማደስ በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ አስጀምሯል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በማስጀመሪያ  መርሐግብሩ ላይ እንዳሉት  የሀገር ባለውለታዎችን ማክበርና አቅመ ደካሞችን ማገዝ እጅግ አስፈላጊና የመንግስታችን ቀዳሚ ተግባር ነው ብለው በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በከተማችን እየተሰራ ያለውን  የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህልን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

መረዳዳትና መደጋገፍ  የኢትዮጲያኖችን መገለጫ ነው  ያሉት ቢሮ ኃላፊዋ  ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታም ወሳኝ ነው ብለዋል።

 ኃላፊዋ አክለውም  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተሰጠው ተልዕኮና ኃላፊነት በተጨማሪ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን አካቶ በመያዝና በጎ ፈቃደኛኞችን በማስተባበር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አንስተው 
የቢሮው  አንዱ ተግባር የሀይማኖት እሴት ግንባታና  የሀይማኖት ተቋማቶች ከመንግስት ጎን በመሆን  ህዝቡን የመደገፍ  ስራ እንዲሰሩ ማድረግ ሲሆን  በዚህም የልደታ ክ/ከተማ  የእስልማና ምክር ቤቱ  ዛሬ ላስጀመረው  ድጋፍ ምስጋና አቅርበው   ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ነው እንደሚባለው  እርስ በርስ የመደጋገፍ እና የመተባበር  ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ኡስታዝ ሱልጣን ቶሬ  የልደታ ክ/ከተማ የእምነት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢና የእስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ በእስልምና አስተምሮ አንዱ አቅመ ደካሞችን መርዳትና መደገፍ ነው ብለው ዛሬ በልደታ ክ/ከተማ ያስጀመሩትን የአራት አባውራ የመኖሪያ ቤት  ዕድሳት  በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለነዋሪዎቹ እንደሚያስረክቡና   በቀጣይም  የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ተሳትፎአቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልፀዋል።

ዛሬ  በልደታ ክ/ከተማ የተጀመረው የአራት አባውራ የመኖሪያ ቤት ዕድሳት  በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለነዋሪዎቹ  እንደሚተላለፍ ተገልጿል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157