ከተማችን ላይ ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ለማስቀጠል...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ከተማችን ላይ ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ለማስቀጠል በቅንጅትና በመናበብ በትኩረት መስራት ይገባል።

ከተማችን ላይ ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ለማስቀጠል በቅንጅትና በመናበብ በትኩረት መስራት ይገባል።

     አቶ ፍስሀ ጥበቡ 
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራን በማጠናከር የከተማዋን ዘላቂ ሰላም እያረጋገጠና የህግ የበላይነትን እያሰፈነ ይገኛል። ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዛሬ በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የአንድ ማእከል የሰላም ሰራዊት ስምሪት ተሰጥቷል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስምሪት አሰጣጡ ላይ ተገኝተው  እንዳሉት ስኬታማ የፀጥታ ስራ የሚገነባው በቅንጅት፣ በተጠያቂነት፣ በትጋት እና በህዝብ እምነት ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ነው።

ኃላፊው አክለውም የፀጥታ ስራ የአንድ ተቋም  ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም የጋራ ተግባር  ውጤት ነው ብለው  ሁሉም የከተማችን ነዋሪ  ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር፣  የፀጥታ አካሉም ከማህበረሰቡ ጋር በመቀራረብ እና ህግን መሠረት  በማድረግ አሁን ላይ በከተማችን ያለውን ሰላም ማፅናትና ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በስምሪት አሰጣጡ ላይ እንደተመላከተው በከተማችን ሰላምና ፀጥታን ማጠናከር፣ የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ህግን ማስከበር እና ዜጎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በሰላም እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

የከተማ ፣ የክ/ከተማና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች ፣ የፀጥታ አካላትና የሰላም ሰራዊት በስምሪቱ ላይ ተገኝተዋል።

ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

📞 የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7977157